እርቅ ከእራስ!
መቼስ እኛ ሰዎች ስንባል አንዱ መተዳደርያ ደንባችን በትንሹም በትልቁም ብስጭትጭት ማለት፣ መነጫነጭ፣ ማማረር የመሳሰሉት ጥቃቅን እና አነስተኛ ባህርያት ናቸው፡፡ እርግጥ ነው ስሜትን መግለጽ ሰውኛ ነው፡፡ ግን ደግሞ የእኛ ልምምድ ትንሽ በዘት ይላል፡፡
መቼስ እኛ ሰዎች ስንባል አንዱ መተዳደርያ ደንባችን በትንሹም በትልቁም ብስጭትጭት ማለት፣ መነጫነጭ፣ ማማረር የመሳሰሉት ጥቃቅን እና አነስተኛ ባህርያት ናቸው፡፡ እርግጥ ነው ስሜትን መግለጽ ሰውኛ ነው፡፡ ግን ደግሞ የእኛ ልምምድ ትንሽ በዘት ይላል፡፡
የዛሬ ጽሑፌ መነሻ ሰሞኑን ከድሮ መ/ቤት ባልደረባዬ የተደወለልኝ ስልክ ነው፡፡ ይህቺ የሥራ ባልደረባዬ ደውላ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ በተለያየ ሚዲያ እያየችኝ እንደሆነ እና እድገቴ እንደሚያስገርማት በመግለጽ አድናቆቷን ካርከፈከፈችልኝ በኋላ ጨዋታውን አደራነው፡፡ አመስግኛት ሳበቃ ስለቤተሰብ፣ ስለ ሥራ ወዘተ ተጠያየቅን፤ ወግ ነውና፡፡ ይህች የቀድሞ የሥራ ባልደረባዬ ስትደውልልኝ ተጠንቅቄ ነው የማናግራት፤ ከቀድሞ ባህርይዋ በመነሳት፡፡ የፈለገውን ዓመት ፈጅቶ ባገኛት ምንም የተሻሻለ የባህርይ ለውጥ የማይታባት ናት፡፡ አሁንም እዚያው ከእኔ በፊት ተቀጥራ የምትሰራበት መ/ቤት እየሠራች መቆየቷ ነው መሰለኝ የተግባቦት ስልቷ አልተለወጠም፡፡ የዚያ መ/ቤቱ ብቻ ሳይሆን የባህርይዋም ታማኝ እና ቅን አገልጋይ እንበላት ይሆን!? በደወለችባቸው ወይም ባገኘኋት አጋጣሚዎች ሁሉ ታጉረመርማለች፡፡
እኛ ሀገር “ከፍትፍቱ ፊቱ” የሚባል አሪፍ አባባል አለ፤ ብዙዎቻችን የምንወደው ይመስለኛል አባባሉን፡፡ እናም በተቻለን መጠን የምንጣጣረው ጥሩ ፊት አላት/አለው እንድንባል ነው፤ እኛም ከሌሎች የምንጠብቀው ይህንኑ ነው፡፡ ፍትፍት ለአባባሉ ድምቀት የተመረጠው እንደሚመስለኝ ያው እኛ ኢትዮጵያውያን ፍትፍት እንወዳለን ምክንያቱም በልተን ያጠግበናል፣ እንደ ሰው በምግብነቱ ቆመን እንሄድ ዘንድ ስለሚጠግነን ነው፡፡
ማረጥ ፀጋ ነው! ርቃቶች አንጋፋዎቹ እድሜ እና ጤና ይስጥሽ/ይስጥህ ናቸው፤ እድሜ ፀጋ ነዋ፣ እድሜ መስታወት ነዋ፣ መኖር ካለመኖር የተሻለ ነዋ! ከዚያ እኛም ስንመረቅ አሜን ብለን እንቀበልና ከኋላ ተከትለው የሚመጡት ነገሮች
አይመቸኝም! “እዬዬም ሲደላ ነው!” ያሉት እነዚያ የድሮ አበዎች ምን ያህል እንደቀደሙን ሳስብ ግርም ይለኛል፡ ከምር ግን የድሮ ዘመን ተረተኞች ትንቢተኛ አይመስሏችሁም!? ይሄ ተረት እኮ ጥግ ድረስ የሄደ ነው፡፡ እዬዬ ከስሜቶች
የምቾት ቀጠና ለዘላለም ይኑርì አንዳንድ ቃላት ከአማርኛ ስያሜያቸው ይልቅ በእንግሊዝኛ ተለማምደናቸዋል፡፡ የምቾት ቀጠና በእንግሊዝኛው comfort zone በሚል የምናውቀው ነው፡፡ ወደ ዝርዝር ሀሳቡ ከመግባቴ በፊት በትርጉም መጀመሬ ፈገግ አስባለኝ፤ ሁለተኛው መጽሐፌ
የምቾት ቀጠና ለዘላለም ይኑርì Read More »
የሥራ ቦታ የጨዋታ ሜዳ ነው! በሥራ ቅጥር ሕይወቴ ያሳለፍኩትን ጣፋጭ እና ጎምዛዛ ዘመን የመጀመርያው እና “የሕይወቴ ቅኝት” የሚል ርእስ የጻፍኩትን መጽሐፌን ለእራሴም ለአንባቢዎቼም ማስነበቤን እንደ ትልቅ ጀብዱ እቆጥረዋለሁ፡፡ ምክንያቱም ሁላችንም
የሥራ ቦታ የጨዋታ ሜዳ ነው! Read More »
አግቢ! የእኛ ማህበረሰብ መቼስ ደግ ነው! ይሄ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ አንዳንዴ ግን ደግ የማይሆንባቸው ጉዳዮች አሉ፡፡ እንደማህበረሰብ ነው የማወራው እና በጅምላ ጭፍጨፋ እንዳይመስልብኝ ልጠነቀቅ ፈልጌ ነበር፤ ግን በዚህ ጉዳይ ላይ
መቼስ የእኛ ዘመን ከእናቶቻችን ዘመን የተሻለ ነው፡፡ የልጆቻችን ደግሞ ከእኛ የተሻለ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡
ብርቱካን ያስጠላው ብርቱካናማ እንቅስቃሴ! Read More »
አንድ የሙያ ስልጠና የመውሰድ እድል ገጥሞኝ ከዚህ ቀደም በየትኛውም የሕይወት መስመር አግኝቻቸው ከማላውቅ ሴቶች እና ወንዶች ጋር ለሁለት ቀናት አሳልፌ ነበር፡፡