Blog

ሚዛን አይዝመም!

በማለዳ ስልክ ሲደወል አልወድም፡፡ እናቴ ነብሷን ይማረውና በጠዋት ሲደወልላት “ደግሞ ማን ሞተ ሊሉኝ ነው?” እያለች ነበር የምታነሳው እና እንዳጋጣሚ ደግሞ ሁሉም የማለዳ ስልኮች የሞት ዜና እንዳልነበሩ አስታውሳለሁ፡፡ እንደዚያም ሆኖ ግን በቃ የድሮ የእናቴ ስሜት ተጋብቶብኝ አልለቀቀኝም፡፡ ታድያ የፈራሁት የሆነው ለጥቅምት 7 አጥብያ ከሳምንታት በፊት ለባለቤቴ በእጅ ስልኩ ላይ ተደውሎ ነው፡፡ ቀደም ሲል በማናውቀው ቁጥር ደዋይ ለባለቤቴ በማለዳ ከ11 ሰዓት በፊት ደወለ እናም ባናቀውም ማንሳት ነበረበት፡፡ ባለቤቴ በወጣትነቱ የወለዳት ልጅ ነበረችው እናም ደዋይ የእሷን ስም ጠርቶ አባቷ መሆኑን ጠየቀው፡፡ ባለቤቴም እንደ ሕጻን እየተኮላተፈ “አዎ ነኝ፤ ምን ሆነች??” ብሎ ጠየቀ፡፡ “ልቤን እያለች ነውና ቶሎ ድረሱላት” ሲለው በቃ የሆነውን እንዴት ልቀጥልላችሁ፡፡ ፒጃማችን ላይ የቀን ልብስ ደርበን ነበር በፍጥነት እያሽከረከርን የደረስነው፤ “ልቤን ወጋኝ” ብላ ለሆስፒታል እንኳን ሳትደርስ ሕይወቷ አልፎ ነበር እኛ የደረስነው፡፡

ሚዛን አይዝመም! Read More »

The Things We Swallow

In my life, there have been people, situations, and moments that reinforced my own diffidence about speaking verbally about how I felt. During periods of tension with my siblings or friends, I wrote letters. In my personal relationships, I found comfort in text messages rather than phone calls to hash things out.

The Things We Swallow Read More »

The እኩያን

ልጅትን ያወቅኳት በማህበራዊ ሚዲያ ነው፡፡ በአካል እንድታገኘኝ ደጋግማ ስትወተውተኝ “ያስጨነቃትን ነገር ለእኔ በመንገር ቀለል የሚላት ከሆነ የመገኘት መስዋእትነት ልክፈል” ብዬ ሰዓቴን ገድቤ ቀጠርኳት፡፡ ገደብ ያደረግኩት ያንን ያህል ከአቅም በላይ የሆነ ውጥረት ውስጥ ስለሆንኩ ሳይሆን “ብዙም ከማላውቃት ሴት ጋር ከዚያ በላይ ምንም መነጋገር አልችልም” ብዬ አስቀድሜ በመደምደሜ ነበር፡፡

The እኩያን Read More »

The Grammar of Healing: Art in Transitional Justice

Last Month, Studio 11 Art Gallery hosted a profound conversation alongside the exhibition Grammar of Healing. Survivors of grave human rights violations entrusted their stories to artists, who translated them into paintings, sculptures, and drawings. The exhibition became an artistic showcase; a living archive of pain, resilience, and hope. Against this backdrop, the Association of Ethiopian Human Rights invited three panelists: a human rights expert, an art professor, and myself, a psychologist, to explore the role of art in transitional justice.

The Grammar of Healing: Art in Transitional Justice Read More »

Bonne annee!

New year, new me. Resolutions are just an excuse to feel brand new when we know that nothing has changed, really; just another day with a different number. Still, we love to find hope in anything, as long as it makes us feel good.

Bonne annee! Read More »

ወይኔ ጉዴ ፈላ!

በቀደም እለት አዲስ ዓመት የነበረው 2018 ዓ.ም. ከምኔው ተሯሩጦ አልቆ አሮጌ እንደሆነ አልገረማችሁም!? ደግሞ እኮ እራሱን ችሎ ቢያረጅ እኛ ምን ቸግሮን! አባሪ ተባባሪ አድርጎ እኛንም ማስከተሉ ከፋ እንጂ፡፡ ለነገሩ በዚህ መኖር ተአምር በሆነበት ዘመን እየኖሩ ማርጀት እኮ ፀጋ ነው፡፡ ጥያቄው ግን እየኖርን በጊዜው ያቀድነውን ለመከወን እድል አግኝተን ይሆን ወይ? የሚለው ነው፡፡ የጊዜው ሩጫ እንደ ድሮ አይመስለኝም፡፡ አንዳንዴ ነዳጅ ልቀዳ ነዳጅ ማደያ ስቆም ማሽኑ ሲከፈት  ቁጥሮቹን በቅጡ ሳላያቸው የነዳጅ መጠን ማሳያ (ጌጅ) ጋኑ መሙላቱን የሚያሳየው ፍጥነት እና የጊዜ መሮጥ ይመሳሰሉብኛል፡፡ እናንተስ!? እንደ እኔ ነው የሚሰማችሁ ወይንስ ጊዜው አላልቅ እያለ አዲስ አመት እየናፈቃችሁ ነው? ያው ለሁላችንም አዲስ አመት መጣሁላችሁ እያለን ነውና እኛም እንኳን ደህና መጣህ እንለዋለን፡፡

ወይኔ ጉዴ ፈላ! Read More »

The Other Side

The position you’re in right now is most probably determined by all the choices you’ve made up until this point. The people you surround yourself with, the degree you’ve gotten, your parents, your siblings, the environment you grew up in, the things you’ve been exposed to—you get the gist. And the position you will be in the future is also determined by those things, carefully curated into the stereotype of your kind of people.

The Other Side Read More »

አይነኬ!

በአንድ ወቅት እሰራበት የነበረ መ/ቤት ውስጥ እንደልቡ እንዲሆን ልዩ መታወቅያ የተሰጠው የሚመስል  የስራ ባልደረባችን ነበር፡፡ ታድያ ይሄ ሰው አለቃ ከምንዝር ሳይለይ ሁሉንም ሰው አፉ ያመጣለትን ሲናገር ልቡን እንኳን የሚያማክር አይመስለኝም፡፡ ብዙ የማይረሱኝ አስከፊ፣ አናዳጅ እና አንዳንዴም አስገራሚ የሆኑ ንግግሮቹ ከነስሜታቸው በአእምሮዬ ተቀርፀው ቀርተዋል፡፡ ከማይረሱኝ ንግግሮቹ ለምሳሌ አንዱን ላጋራችሁ፤ የስራ ኃላፊያችን የብዙ ልጆቻቸው እናት ከነበሩት የ80 ሚስታቸው ተደብቀው በቢሮ ውስጥ በፈጠሩት ጾታዊ ግንኙነት አንድ ልጅ ወለዱ እና ያቺን ያስወለዷትን ሴት ለመካስ ከነበረችበት ዝቅተኛ የስራ መደብ ከፍ አስደርገው እሳቸው በኃላፊነት በሚመሩት እና እኛ የምንሰራበት ክፍል አስመድበዋት ነበር፡፡ ድርጊቱ ድብቅ ይሁን እንጂ ሰራተኛው ሁሉ በጭምጭምታ እየተቀባበለ አውቆታል፤ ግን ማንም ምንም አይናገርም ነበር፡፡ ታድያ በአንዱ ቀን ያቺ እናት ልጇን የመ/ቤቱ ክሊኒክ ለማሳከም ታመጣ እና ምርመራው ካለቀ በኋላ ቢሮ ይዛው ትመጣለች፡፡ ያ እንደልቡ የሚናገረው ባልደረባችን  ሰራተኛው ሰብሰብ ባለበት ልጁን ለመሳም ሳብ እያደረገ “አንበሳው ምናለ እናትህን እንኳን ብትመስል! ከማርገዟ በስተቀር እናትነቷን የሚያረጋግጥ አንድ ነገር እንኳን የላትም እኮ፤ ይሄኔ እነዚያ ከቤት የተወለዱት ልጆቹ እንዲህ እንደ አንተ ቁርጥ አባታቸውን አይመስሉም እኮ!” በማለቱ እኛ ተሳቀቅን እንጂ እሱ ምንም አልመሰለው፡፡ አለቃችን ሽምቅቅ እሷ ደግሞ ቁጥት ቢሉም ቃል አላወጡም፡፡ “አሁንስ አበቃለት!” ያልነው ያ እንደልቡ ተናጋሪ ሰራተኛ በማግስቱ ከኣለቃችን ጋር በወቅቱ ያካሄድ ስለነበረው የአፍሪካ ዋንጫ የእግር ኳስ  ቅልጥ ያለ ጭውውት ሲያደርጉ ስሰማቸው “ወንዶች ስለሆኑ ነው እንደልቡ ተናግሮ ያልተኮራረፉት?” ብዬ በሀሳቤ ሳውጠነጥን ሰውየው ለካ አይነኬ ስለሆነ ነው፡፡ እሱ ጋር ያለን ምስጢር ለመጠበቅ ባላየ ይታለፋል፡፡ ታድያ በየመ/ቤቱ እንደዚህ ያሉ ስለስራም ይሁን ስለሰዎች ግላዊ ሕይወት የመሰላቸውን የሚናገሩ ሰራተኞች ገጥመውኛል፤ ግን ማንም ምንም አይላቸውም በቃ አይነኬ ናቸው፡፡ እኔ ዛሬ ላይ ቆሜ ሳስታውሳቸው ግን ግርም ድንቅ ይለኛል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ አይነኬዎች መጠቀሚያዎች ስለሆኑ ነው፡፡

አይነኬ! Read More »

There is no I without WE

Loneliness is a global epidemic affecting one in six people and linked to 100 deaths every hour, according to research. In the past, I’ve argued that it’s better to be lonely than to seek attention and validation from others. This time, however, I would like to play devil’s advocate and offer us a new perspective.

There is no I without WE Read More »

Scroll to Top