Fitsum Atnafekework

conference

ትልቁ ኮንፈረንስ!

በሕይወቴ ብዙ የመጀመርያ እና አስደናቂ የሚባሉ ገጠመኞች ሞልተውኛል፤ በአብዛኛው ድንቅ የሚባሉ ሲሆኑ በተቃራኒውም ድንቅ ያልሆኑ ገጠመኞች አሉኝ፡፡ መጀመርያ ድንቅ ያልሆነውን አንዱን ልተርክላችሁ፡፡ ለረዥም ዓመታት የሰራሁበት እና በተለይ በወጣትነቴ ብዙ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ በማገልገል የምታወቅበት መሥሪያ ቤት በወቅቱ መሀከለኛው የአመራር ደረጃ ላይ ለነበርነው ኃላፊዎች በአውሮፓ ሀገራት የልምድ መጋራት እና የአጭር ስልጠና እድል ይሰጥ ነበር፡፡

እርቅ ከእራስ!

መቼስ እኛ ሰዎች ስንባል አንዱ መተዳደርያ ደንባችን በትንሹም በትልቁም ብስጭትጭት ማለት፣ መነጫነጭ፣ ማማረር የመሳሰሉት ጥቃቅን እና አነስተኛ ባህርያት ናቸው፡፡ እርግጥ ነው ስሜትን መግለጽ ሰውኛ ነው፡፡ ግን ደግሞ የእኛ ልምምድ ትንሽ በዘት ይላል፡፡

ለውጥማ ያስፈራል!

የዛሬ ጽሑፌ መነሻ ሰሞኑን ከድሮ መ/ቤት ባልደረባዬ የተደወለልኝ ስልክ ነው፡፡ ይህቺ የሥራ ባልደረባዬ ደውላ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ በተለያየ ሚዲያ እያየችኝ እንደሆነ እና እድገቴ እንደሚያስገርማት በመግለጽ አድናቆቷን ካርከፈከፈችልኝ በኋላ ጨዋታውን አደራነው፡፡ አመስግኛት ሳበቃ ስለቤተሰብ፣ ስለ ሥራ ወዘተ ተጠያየቅን፤ ወግ ነውና፡፡ ይህች የቀድሞ የሥራ ባልደረባዬ ስትደውልልኝ ተጠንቅቄ ነው የማናግራት፤ ከቀድሞ ባህርይዋ በመነሳት፡፡ የፈለገውን ዓመት ፈጅቶ ባገኛት ምንም የተሻሻለ የባህርይ ለውጥ የማይታባት ናት፡፡ አሁንም እዚያው ከእኔ በፊት ተቀጥራ የምትሰራበት መ/ቤት እየሠራች መቆየቷ ነው መሰለኝ የተግባቦት ስልቷ አልተለወጠም፡፡ የዚያ መ/ቤቱ ብቻ ሳይሆን የባህርይዋም ታማኝ እና ቅን አገልጋይ እንበላት ይሆን!? በደወለችባቸው ወይም ባገኘኋት አጋጣሚዎች ሁሉ ታጉረመርማለች፡፡

ሴትየዋ!

እኛ ሀገር “ከፍትፍቱ ፊቱ” የሚባል አሪፍ አባባል አለ፤ ብዙዎቻችን የምንወደው ይመስለኛል አባባሉን፡፡ እናም በተቻለን መጠን የምንጣጣረው ጥሩ ፊት አላት/አለው እንድንባል ነው፤ እኛም ከሌሎች የምንጠብቀው ይህንኑ ነው፡፡  ፍትፍት ለአባባሉ ድምቀት የተመረጠው እንደሚመስለኝ ያው እኛ ኢትዮጵያውያን ፍትፍት እንወዳለን ምክንያቱም በልተን ያጠግበናል፣ እንደ ሰው በምግብነቱ ቆመን እንሄድ ዘንድ ስለሚጠግነን ነው፡፡

ማረጥ ፀጋ ነው!

ማረጥ ፀጋ ነው! ርቃቶች አንጋፋዎቹ እድሜ እና ጤና ይስጥሽ/ይስጥህ ናቸው፤ እድሜ ፀጋ ነዋ፣ እድሜ መስታወት ነዋ፣ መኖር ካለመኖር የተሻለ ነዋ! ከዚያ እኛም ስንመረቅ አሜን ብለን እንቀበልና ከኋላ ተከትለው የሚመጡት ነገሮች

አይመቸኝም!

አይመቸኝም!  “እዬዬም ሲደላ ነው!” ያሉት እነዚያ የድሮ አበዎች ምን ያህል እንደቀደሙን ሳስብ ግርም ይለኛል፡ ከምር ግን የድሮ ዘመን ተረተኞች ትንቢተኛ አይመስሏችሁም!? ይሄ ተረት እኮ ጥግ ድረስ የሄደ ነው፡፡ እዬዬ ከስሜቶች …

አይመቸኝም! Read More »

የምቾት ቀጠና ለዘላለም ይኑርì

የምቾት ቀጠና ለዘላለም ይኑርì አንዳንድ ቃላት ከአማርኛ ስያሜያቸው ይልቅ በእንግሊዝኛ ተለማምደናቸዋል፡፡ የምቾት ቀጠና በእንግሊዝኛው comfort zone በሚል የምናውቀው ነው፡፡ ወደ ዝርዝር ሀሳቡ ከመግባቴ በፊት በትርጉም መጀመሬ ፈገግ አስባለኝ፤ ሁለተኛው መጽሐፌ …

የምቾት ቀጠና ለዘላለም ይኑርì Read More »

Group of coworkers working. Two are high fiving

የሥራ ቦታ የጨዋታ ሜዳ ነው!

የሥራ ቦታ የጨዋታ ሜዳ ነው! በሥራ ቅጥር ሕይወቴ ያሳለፍኩትን ጣፋጭ እና ጎምዛዛ ዘመን የመጀመርያው እና “የሕይወቴ ቅኝት” የሚል ርእስ የጻፍኩትን መጽሐፌን ለእራሴም ለአንባቢዎቼም ማስነበቤን እንደ ትልቅ ጀብዱ እቆጥረዋለሁ፡፡ ምክንያቱም ሁላችንም …

የሥራ ቦታ የጨዋታ ሜዳ ነው! Read More »

Thank you so much for giving me advice that i did not ask for [or want]...

አግቢ!

አግቢ! የእኛ ማህበረሰብ መቼስ ደግ ነው! ይሄ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ አንዳንዴ ግን ደግ የማይሆንባቸው ጉዳዮች አሉ፡፡ እንደማህበረሰብ ነው የማወራው እና በጅምላ ጭፍጨፋ እንዳይመስልብኝ ልጠነቀቅ ፈልጌ ነበር፤ ግን በዚህ ጉዳይ ላይ …

አግቢ! Read More »