አለቃ ወይንስ መሪ?!
አለቃ ወይንስ መሪ?! Image source: https://dannyspina.com/images/blog/leadership_ego/leadership_meme.webp አለቃ (Boss) የሚለው አጠራር የሚያስደስታቸው ብዙ ሰዎች እንዳሉ ተረድቻለሁ፡፡ አለቃ እየተባሉ ሰዎችን መጋበዝ፣ በሰዎች መከበብ፣ ተደማጭነት ማግኘት፣ ተከታይ መፍራት፣ አዛዥ ናዛዥ (ናዛዥ ግን ምንድነው!?) […]
አለቃ ወይንስ መሪ?! Image source: https://dannyspina.com/images/blog/leadership_ego/leadership_meme.webp አለቃ (Boss) የሚለው አጠራር የሚያስደስታቸው ብዙ ሰዎች እንዳሉ ተረድቻለሁ፡፡ አለቃ እየተባሉ ሰዎችን መጋበዝ፣ በሰዎች መከበብ፣ ተደማጭነት ማግኘት፣ ተከታይ መፍራት፣ አዛዥ ናዛዥ (ናዛዥ ግን ምንድነው!?) […]
ሕይወትን በሁለት ትላልቅ ምእራፎች ከፍለን እንድናወጋ ፈለግሁ እና ይህንን ጽሑፍ ጫር ጫር አደረግሁ፤ የሚመለከተንም የማይመለከተንም ካነበብን በኋላ የእኛ ሕይወት የቱ ጋር እንደሆነ ቆም ብለን እንድናይ ያመላክተናል ብዬ አምናለሁ፡፡
እንደ ሀገር ብዙ ጥሩ ጥሩ የሆኑ ባህሎች እና ትውፊቶች ያሉን ዜጎች ነን፡፡ እንደ ሰው የምንረዳዳባቸው የምንደጋገፍባቸው አበረታች የሆኑ እሴቶቻችን የትዬለሌ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን ኑሮ ቢከፋ (ቢወደድብን) “ከእኔ ችግር የእነሱ ይብሳል” ብሎ የተቸገሩትን የሚዳብሱ እና የሚያጎርሱ ዜጎች ያለባት ሀገር ናት፣ ኢትዮጵያ፡፡
አንዲት የኤውብ ቤተሰብ የሆነች እህት ስልክ ደወለችልኝ እና “እስቲ ስለ ሴት የተተረቱ አዎንታዊ አባባሎች ንገሪኝ?” አለችኝ፡፡ ጥያቄው ቅጽበታዊ ቢሆንም ጊዜ ወስጄ ባወጣና ባወርድ በቶሎ ሊመጣልኝ አልቻለም፡፡
ስለ ሴት መልካም አባባሎች!? Read More »
አንድ ቀን እለት አንድ ሆስፒታል ውስጥ ቁጭ ብዬ ተራ እየጠበቅሁ ሳለሁ ዘለግ ያለች ሴት የተጫማችውን ነጠላ ጫማ በድካም ስሜት እየጎተተች መጥታ ፊት ለፊቴ ተቀመጠች፡፡ ፊቷ አዲስ አልሆነብኝም፤ ግን ደግሞ እሷ ፊት ላይ ምንም “የት ነው የማውቃት?” መደናገር ስላላየሁባት የመልክ መመሳሰል አድርጌ ወስጄው በዝምታ እያለሁ ለየት ያለው ስሟ ከነአባቷ ሲጠራ ግምቴ ልክ እንደነበረ አመንኩ፡፡
ምን ሆነ መሰላችሁ! ሰሞኑን አንድ የቤተሰብ የምሳ ግብዛ ላይ አንድ ወጣት በትህትና ሲያስተናግድ ቆይቶ ለመሄድ ሊሰናበት ሲል ግብዣውን ያዘጋጁት ታላቅ ሰው ልጁን ለታዳሚዎች ማስተዋወቅ ፈለጉ፡፡ በጣም ጥሩ ልብ ያለው ልጅ መሆኑን፣ የዩኒቨርስቲ ምሩቅ መሆኑን እና ድግሱንም በደንብ ያገዘ መሆኑን አስተዋወቁና እስቲ እራስህን አስተዋውቃቸው በማለት እድሉን ሰጡት፡፡
ማህበራዊ ኃላፊነት እና የእራስ ኃላፊነት Read More »
ማህበራዊ ሚዲያ (social media) ተጠቃሚ ከሚባሉ ሰዎች አንዷ ነኝ፡፡ በተለይ ፌስቡክ በጣም ጊዜ ካጣሁ እንኳን በቀን አንዴ ገብቼ ትንሽ መልእክት እጽፋለሁ፤ የሌሎችን ጽሑፎች አነባሁ፤ ሀሳብ እሰጣለሁ፣ እቀበላለሁም፡፡ ብዙ ሰዎች ፌስቡክን የስራ-ፈት ሚዲያ አድርገው ስለሚቆጥሩት እንደተዉት ሲናገሩ እሰማለሁ፡፡ እኔ ደግሞ በተቃራኒው ምንያህል እየተጠቀምኩበት እንደሆነ ቤቴ ይቁጠረው፡፡
እድገታችን የሚለው ቃል ሁላችንንም በሀሳብ በየአቅጣጫው እንደወሰደን አልጠራጠርም፡፡ የቱን እድገት ይሆን ደግሞ ዛሬ የምታወራልን፤ የሀገራችንን? የልጅነታችንን? የድርጅታችንን? እድገት በየፈርጁ በአእምሯን ውስጥ ተመላለሰ አይደል! እኔ ግን ማውራት የፈለግኩት የስራ ቦታ እድገት (promotion) ነው፡፡
ስኬታማ ሴቶች የሆኑትን የሆኑት ብዙ ወድቀውና ተነስተው ነው! ለነገሩ ሴቶች ብቻ ሳይሆኑ ወንዶችም ጭምር፡፡ የእኔ ነገር በቀላሉ ሰዎች ብዬ እኮ ማጠቃለል እችል ነበር አይደል! ግን ማውራት የፈለግኩት ስለስኬታማ ሴቶች ገመና ነውና ነው፡፡ ወንዶች ስኬታማ ሲሆኑ ጎበዝ ነው፣ ባለሀብት ነው፣ ታድሎ፣ ከምን ተነስቶ ይሆን እዚህ የደረሰው፣ ወዘተ የመሳሰሉት እሱና እሱ ላይ ያተኮሩ አስተያየቶች እና አድናቆቶች ሲሰጡ ከመስማት ያለፈ ብዙም ስለ እሱ (ስለስኬታማው ሰውዬ) ግላዊ ማንነት ገፋ ተደርጎ ሲጠየቅ ወይንም ሲወራ አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ ቢጠየቅም ለአመል እንጂ ያንን ያህል እርቀት አይኬድም፡፡
በሕይወቴ ብዙ የመጀመርያ እና አስደናቂ የሚባሉ ገጠመኞች ሞልተውኛል፤ በአብዛኛው ድንቅ የሚባሉ ሲሆኑ በተቃራኒውም ድንቅ ያልሆኑ ገጠመኞች አሉኝ፡፡ መጀመርያ ድንቅ ያልሆነውን አንዱን ልተርክላችሁ፡፡ ለረዥም ዓመታት የሰራሁበት እና በተለይ በወጣትነቴ ብዙ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ በማገልገል የምታወቅበት መሥሪያ ቤት በወቅቱ መሀከለኛው የአመራር ደረጃ ላይ ለነበርነው ኃላፊዎች በአውሮፓ ሀገራት የልምድ መጋራት እና የአጭር ስልጠና እድል ይሰጥ ነበር፡፡