Fitsum Atnafekework

ተጋልጠናል!

ማህበራዊ ሚዲያ (social media) ተጠቃሚ ከሚባሉ ሰዎች አንዷ ነኝ፡፡ በተለይ ፌስቡክ በጣም ጊዜ ካጣሁ እንኳን በቀን አንዴ ገብቼ ትንሽ መልእክት እጽፋለሁ፤ የሌሎችን ጽሑፎች አነባሁ፤ ሀሳብ እሰጣለሁ፣ እቀበላለሁም፡፡ ብዙ ሰዎች ፌስቡክን የስራ-ፈት ሚዲያ አድርገው ስለሚቆጥሩት እንደተዉት ሲናገሩ እሰማለሁ፡፡ እኔ ደግሞ በተቃራኒው ምንያህል እየተጠቀምኩበት እንደሆነ ቤቴ ይቁጠረው፡፡

ተጋልጠናል! Read More »

የእድገታችን ምስጢር?

እድገታችን የሚለው ቃል ሁላችንንም በሀሳብ በየአቅጣጫው እንደወሰደን አልጠራጠርም፡፡ የቱን እድገት ይሆን ደግሞ ዛሬ የምታወራልን፤ የሀገራችንን? የልጅነታችንን? የድርጅታችንን? እድገት በየፈርጁ በአእምሯን ውስጥ ተመላለሰ አይደል! እኔ ግን ማውራት የፈለግኩት የስራ ቦታ እድገት (promotion) ነው፡፡

የእድገታችን ምስጢር? Read More »

አግብታለች?

ስኬታማ ሴቶች የሆኑትን የሆኑት ብዙ ወድቀውና ተነስተው ነው! ለነገሩ ሴቶች ብቻ ሳይሆኑ ወንዶችም ጭምር፡፡ የእኔ ነገር በቀላሉ ሰዎች ብዬ እኮ ማጠቃለል እችል ነበር አይደል! ግን ማውራት የፈለግኩት ስለስኬታማ ሴቶች ገመና ነውና ነው፡፡ ወንዶች ስኬታማ ሲሆኑ ጎበዝ ነው፣ ባለሀብት ነው፣ ታድሎ፣ ከምን ተነስቶ ይሆን እዚህ የደረሰው፣ ወዘተ የመሳሰሉት እሱና እሱ ላይ ያተኮሩ አስተያየቶች እና አድናቆቶች ሲሰጡ ከመስማት ያለፈ ብዙም ስለ እሱ (ስለስኬታማው ሰውዬ) ግላዊ ማንነት ገፋ ተደርጎ ሲጠየቅ ወይንም ሲወራ አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ ቢጠየቅም ለአመል እንጂ ያንን ያህል እርቀት አይኬድም፡፡

አግብታለች? Read More »

conference

ትልቁ ኮንፈረንስ!

በሕይወቴ ብዙ የመጀመርያ እና አስደናቂ የሚባሉ ገጠመኞች ሞልተውኛል፤ በአብዛኛው ድንቅ የሚባሉ ሲሆኑ በተቃራኒውም ድንቅ ያልሆኑ ገጠመኞች አሉኝ፡፡ መጀመርያ ድንቅ ያልሆነውን አንዱን ልተርክላችሁ፡፡ ለረዥም ዓመታት የሰራሁበት እና በተለይ በወጣትነቴ ብዙ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ በማገልገል የምታወቅበት መሥሪያ ቤት በወቅቱ መሀከለኛው የአመራር ደረጃ ላይ ለነበርነው ኃላፊዎች በአውሮፓ ሀገራት የልምድ መጋራት እና የአጭር ስልጠና እድል ይሰጥ ነበር፡፡

ትልቁ ኮንፈረንስ! Read More »

እርቅ ከእራስ!

መቼስ እኛ ሰዎች ስንባል አንዱ መተዳደርያ ደንባችን በትንሹም በትልቁም ብስጭትጭት ማለት፣ መነጫነጭ፣ ማማረር የመሳሰሉት ጥቃቅን እና አነስተኛ ባህርያት ናቸው፡፡ እርግጥ ነው ስሜትን መግለጽ ሰውኛ ነው፡፡ ግን ደግሞ የእኛ ልምምድ ትንሽ በዘት ይላል፡፡

እርቅ ከእራስ! Read More »

ለውጥማ ያስፈራል!

የዛሬ ጽሑፌ መነሻ ሰሞኑን ከድሮ መ/ቤት ባልደረባዬ የተደወለልኝ ስልክ ነው፡፡ ይህቺ የሥራ ባልደረባዬ ደውላ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ በተለያየ ሚዲያ እያየችኝ እንደሆነ እና እድገቴ እንደሚያስገርማት በመግለጽ አድናቆቷን ካርከፈከፈችልኝ በኋላ ጨዋታውን አደራነው፡፡ አመስግኛት ሳበቃ ስለቤተሰብ፣ ስለ ሥራ ወዘተ ተጠያየቅን፤ ወግ ነውና፡፡ ይህች የቀድሞ የሥራ ባልደረባዬ ስትደውልልኝ ተጠንቅቄ ነው የማናግራት፤ ከቀድሞ ባህርይዋ በመነሳት፡፡ የፈለገውን ዓመት ፈጅቶ ባገኛት ምንም የተሻሻለ የባህርይ ለውጥ የማይታባት ናት፡፡ አሁንም እዚያው ከእኔ በፊት ተቀጥራ የምትሰራበት መ/ቤት እየሠራች መቆየቷ ነው መሰለኝ የተግባቦት ስልቷ አልተለወጠም፡፡ የዚያ መ/ቤቱ ብቻ ሳይሆን የባህርይዋም ታማኝ እና ቅን አገልጋይ እንበላት ይሆን!? በደወለችባቸው ወይም ባገኘኋት አጋጣሚዎች ሁሉ ታጉረመርማለች፡፡

ለውጥማ ያስፈራል! Read More »

ሴትየዋ!

እኛ ሀገር “ከፍትፍቱ ፊቱ” የሚባል አሪፍ አባባል አለ፤ ብዙዎቻችን የምንወደው ይመስለኛል አባባሉን፡፡ እናም በተቻለን መጠን የምንጣጣረው ጥሩ ፊት አላት/አለው እንድንባል ነው፤ እኛም ከሌሎች የምንጠብቀው ይህንኑ ነው፡፡  ፍትፍት ለአባባሉ ድምቀት የተመረጠው እንደሚመስለኝ ያው እኛ ኢትዮጵያውያን ፍትፍት እንወዳለን ምክንያቱም በልተን ያጠግበናል፣ እንደ ሰው በምግብነቱ ቆመን እንሄድ ዘንድ ስለሚጠግነን ነው፡፡

ሴትየዋ! Read More »

ማረጥ ፀጋ ነው!

ማረጥ ፀጋ ነው! ርቃቶች አንጋፋዎቹ እድሜ እና ጤና ይስጥሽ/ይስጥህ ናቸው፤ እድሜ ፀጋ ነዋ፣ እድሜ መስታወት ነዋ፣ መኖር ካለመኖር የተሻለ ነዋ! ከዚያ እኛም ስንመረቅ አሜን ብለን እንቀበልና ከኋላ ተከትለው የሚመጡት ነገሮች

ማረጥ ፀጋ ነው! Read More »

አይመቸኝም!

አይመቸኝም!  “እዬዬም ሲደላ ነው!” ያሉት እነዚያ የድሮ አበዎች ምን ያህል እንደቀደሙን ሳስብ ግርም ይለኛል፡ ከምር ግን የድሮ ዘመን ተረተኞች ትንቢተኛ አይመስሏችሁም!? ይሄ ተረት እኮ ጥግ ድረስ የሄደ ነው፡፡ እዬዬ ከስሜቶች

አይመቸኝም! Read More »

የምቾት ቀጠና ለዘላለም ይኑርì

የምቾት ቀጠና ለዘላለም ይኑርì አንዳንድ ቃላት ከአማርኛ ስያሜያቸው ይልቅ በእንግሊዝኛ ተለማምደናቸዋል፡፡ የምቾት ቀጠና በእንግሊዝኛው comfort zone በሚል የምናውቀው ነው፡፡ ወደ ዝርዝር ሀሳቡ ከመግባቴ በፊት በትርጉም መጀመሬ ፈገግ አስባለኝ፤ ሁለተኛው መጽሐፌ

የምቾት ቀጠና ለዘላለም ይኑርì Read More »

Scroll to Top