Fitsum Atnafekework

አትተኙ!

እስቲ ስንቶቻችሁ ናችሁ “የሕይወቴ ቅኝት” የሚለውን መጽሐፍ ያነበባችሁ? ያላነበባችሁ እንግዲህ ተዋውሳችሁ አንብቡ ምክንያቱም ሁለተኛ እትም ለማሳተም “እቁብ ግቡልኝ?” ብዬ ጓደኞቼን በዚህ ዘመን አላስቸግርም፡፡ ድሮ የእኛ ዘመን፣ የእነሱ ዘመን ስንል አስር ወይንም ሃያ ዓመት ልዩነት እየፈለግን ነበር፤ ምክንያቱም ለውጦች አዝጋሚ (evolutional change) ናቸዋ፡፡ አሁን እኮ ዘመን ወደ ሳምንት ተቀይሯል መሰለኝ ባለፈው ሳምንት የነበረ ዛሬ ተለውጦ ታገኙታላችሁ፡፡ ነገር ሁሉ እንደቤት አስቤዛ ተለዋዋጭ ሆኗል፡፡ የዛሬ ሦስት ዓመት በኤውብ እቁብተኞቼ ድጋፍ አሳትሚያለሁ፡፡ እና ኑሮ ቀልብ ባሳጣበት እና አንባቢ በጠፋበት በዚህ ዘመን ወደ ማተምያ ቤት አልሄድም ለማለት ነው፡፡ ለማንኛውም መጽሐፌን ያነሳሁላችሁ ከዚያ ውስጥ አንዱን ሰበዝ መዝዤ ላወራላችሁ ፈልጌ ነው፡፡

አትተኙ! Read More »

ትዳራችን ኮሽታ የለውምì

ድሮ ወደ ኮሌጅ ልገባ ስል ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወደ ኮሌጅ ለመሄድ የሚያዘጋጅ መጽሐፍ ነው ተብሎ የታመነበትን የሲሳይ ንጉሱ ድርሰት የሆነውን “ሰመመን” አንብቤ እንድዘጋጅ ያደረጉትን የጓደኛዬ የገነት ወንድሞች በሕይወቴ ክብር መዝገብ ላይ ጽፌአቸዋለሁ፡፡ አስባችሁታል ገና ዩኒቨርስቲውን ዋና በር ስትረግጡ በስህተትም ተብላችሁ የማታውቁትን “እንዳንቺ አይነት ቆንጆ ሴት በዚህ ምድር አይቼ አላውቅም!” የሚሏችሁ ሲኒየር ተማሪዎች ሙድ እየያዙባችሁ እንደሆነ አይገባችሁም ነበር እኮ፡፡

ትዳራችን ኮሽታ የለውምì Read More »

እርጉዟን ማን ይቅጠራት!?

እርጉዟን ማን ይቅጠራት!? Image source: https://www.pngegg.com/en/png-besfc/download አንዳንድ የጦፉ ክርክሮች በአንድ ወገን አሸናፊነት ወይም አሳማኝነት ሳይቋጩ ሲቀሩ እንዴት ያንገበግበኛል መሰላችሁ፡፡ በጓደኛሞች ወይም በቤተሰብ መሀከል የሚደረግ ክርክር ወይም ቃሉን የተሻለ ለማድረግ ጭውውት

እርጉዟን ማን ይቅጠራት!? Read More »

ጆሮም እንደ ዓይን መዝጊያ ቢኖረው?!

የሰውነት አካላችን በቅንጅት የሚሰራው ስራ እኛን እኛ ያደርገዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለነገሮች ተጋላጭ የሚያደርገን ፈልገን ሳይሆን ሳንፈልግ ወይንም ከአቅም በላይ በሆነ ክስተት ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ቦታ ሄደን ለተከሰተው ክስተት እግራችን ፈቅዶ ባይሄድ ላናይ ላንሰማ እንችል ነበር፡፡ በሄድንበት ቦታ ዓይናችን “ይሄን ማየት አልፈልግም” ብሎ ከጨፈነ ያንን ክስተት ባለማየት እንተርፋለን ማለት ነው፡፡ እጃችንም ከመንካት ከታቀበ ታቀበ ነው፡፡ ብቻ በአብዛኛው የሰውነታችን ክፍል እምቢ የማለት መብት እስኪኖረው ድረስ ነው የተሰደረው፡፡ አፍንጫ እንኳን እድሜ ለኮቪድ አይባልም እንጂ ልብስ ተሰፍቶለታል፡፡

ጆሮም እንደ ዓይን መዝጊያ ቢኖረው?! Read More »

አለቃ ወይንስ መሪ?!

አለቃ ወይንስ መሪ?! Image source: https://dannyspina.com/images/blog/leadership_ego/leadership_meme.webp አለቃ (Boss) የሚለው አጠራር የሚያስደስታቸው ብዙ ሰዎች እንዳሉ ተረድቻለሁ፡፡ አለቃ እየተባሉ ሰዎችን መጋበዝ፣  በሰዎች መከበብ፣ ተደማጭነት ማግኘት፣ ተከታይ መፍራት፣ አዛዥ ናዛዥ (ናዛዥ ግን ምንድነው!?) 

አለቃ ወይንስ መሪ?! Read More »

ትዳር ለእሷ እና ለእሱ

ሕይወትን በሁለት ትላልቅ ምእራፎች ከፍለን እንድናወጋ ፈለግሁ እና ይህንን ጽሑፍ ጫር ጫር አደረግሁ፤ የሚመለከተንም የማይመለከተንም ካነበብን በኋላ የእኛ ሕይወት የቱ ጋር እንደሆነ ቆም ብለን እንድናይ ያመላክተናል ብዬ አምናለሁ፡፡

ትዳር ለእሷ እና ለእሱ Read More »

ሽፍንፍን!

እንደ ሀገር ብዙ ጥሩ ጥሩ የሆኑ ባህሎች እና ትውፊቶች ያሉን ዜጎች ነን፡፡ እንደ ሰው የምንረዳዳባቸው የምንደጋገፍባቸው አበረታች የሆኑ እሴቶቻችን የትዬለሌ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን ኑሮ ቢከፋ (ቢወደድብን)  “ከእኔ ችግር የእነሱ ይብሳል” ብሎ የተቸገሩትን የሚዳብሱ እና የሚያጎርሱ ዜጎች ያለባት ሀገር ናት፣ ኢትዮጵያ፡፡

ሽፍንፍን! Read More »

የዘራነውን ስንዘረዝር!

አንድ ቀን እለት አንድ ሆስፒታል ውስጥ ቁጭ ብዬ ተራ እየጠበቅሁ ሳለሁ ዘለግ ያለች ሴት የተጫማችውን ነጠላ ጫማ በድካም ስሜት እየጎተተች መጥታ ፊት ለፊቴ ተቀመጠች፡፡ ፊቷ አዲስ አልሆነብኝም፤ ግን ደግሞ እሷ ፊት ላይ ምንም “የት ነው የማውቃት?” መደናገር ስላላየሁባት የመልክ መመሳሰል አድርጌ ወስጄው በዝምታ እያለሁ ለየት ያለው ስሟ ከነአባቷ ሲጠራ ግምቴ ልክ እንደነበረ አመንኩ፡፡

የዘራነውን ስንዘረዝር! Read More »

ማህበራዊ ኃላፊነት እና የእራስ ኃላፊነት

ምን ሆነ መሰላችሁ! ሰሞኑን አንድ የቤተሰብ የምሳ ግብዛ ላይ አንድ ወጣት በትህትና ሲያስተናግድ ቆይቶ ለመሄድ ሊሰናበት ሲል ግብዣውን ያዘጋጁት ታላቅ ሰው ልጁን ለታዳሚዎች ማስተዋወቅ ፈለጉ፡፡ በጣም ጥሩ ልብ ያለው ልጅ መሆኑን፣ የዩኒቨርስቲ ምሩቅ መሆኑን እና ድግሱንም በደንብ ያገዘ መሆኑን አስተዋወቁና እስቲ እራስህን አስተዋውቃቸው በማለት እድሉን ሰጡት፡፡

ማህበራዊ ኃላፊነት እና የእራስ ኃላፊነት Read More »

Scroll to Top