ፖለቲካውን እንጫወተው!
የዛሬ ጽሑፌን መነሻ ሀሳብ የወለደልኝ አብረን ሰርተን ለዓመታት ሳላገኛት ኖረን በቅርብ ቀን ያገኘኋት የሥራ ባልደረባዬ ናት፡፡ ይህቺ ሴት አብረን ስንሠራ በጣም አስገራሚ ባህርይ ነበራት፡፡ በተለይ አለቃ/ኃላፊ ለፀብ ከፈለጋችሁ የመረጃው ምንጭ እሷ እንደምትሆን ከጀርባዋ ይወራ ነበር እና ከሠራተኞች በቡና ወይንም በማንኛውም ሁኔታ ልትቀላቀል ስትመጣ “ጨዋታ ቀይሩ!?” ይባል እንደነበር አልረሳውም፡