እንዴት ራሳችንን ከራሳችን እናድን?

በአለማችን ላይ የሰው ልጅ ለመኖር ከሚያስፈልገው ዋነኛ ነገር ደህንነት ነው። የደህንነት መረጋገጥ ከሌለ በሰላም ውሎ መግባትም ሆነ ለተሻለ ሂወት ማቀድ የቁም ቅዠት እንደሚሆን ግልጽ ነው። ደህንነት እንዲጠበቅ ከአጥሮቻችን መርዘምና በላዩ ላይም አደገኛ አጥር ከማሳሰራችን በደህንነት ካሜራ ሙሉ ጊቢ እስከመቆጣጠር፣ ከረጅም የስልክ የይለፍ ቃል እስከ ሰርቨር ደህንነት ተቆጣጣሪ የኢንሳ መሳሪያዎች፣ መኪና ላይ ከሚገጠሙ የማንቂያ ደውሎች እስከ ታጣቂ ጥበቆች እንዲሁም የመሳሰሉትን መንገዶች እንጠቀማለን። “The delite” ያስቀመጣቸው የአለማችን ዝነኛ ሰዎች ለጠባቂዎቻቸው የሚከፍሉትን የገንዘብ መጠን ከ75000 ዶላር እስከ 1 ሚልዮን ዶላር የሚደርስ የሚድያ ሰዎች ይካተቱበታል። ለምሳሌ ያህል፦

              1. ዴቪድ እና ቪክቶሪያ ቤካም

ታዋቂው የእግር ኳስ ተጫዋች ዴቪድ ቤካም እንዲሁም ባለቤቱ የፋሽን ዲዛይነሯ ቪክቶሪያ ቤካም አመታዊ የደህንነት ጥበቃ ወጪያቸው ከ 1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ነው።

                    1. ጄኔፈር አኒስተን
  • “Friends” በተሰኘው ተከታታይ ድራማ የምናውቃት እውቋ የሆሊውድ ፊልም ተዋናይት ስትሆን 240,000ዶላር በላይ ለግል ጥበቃዎቿ በአመት ትከፍላለች።
                    1. ካይሊ ጄነር
  • ታዋቂው የቤተሰብ ሪያሊቲ ሾው “keeping up with the kardashian” አካል የሆነቸው ካይሊ ጄነር፣ ለደህንነት ጥበቃዋ በአመት ከ 8ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ታደርጋለች።
                                                         ሪሃና

  • በልዩ እና ሁለገብ ድምጽዋ የምናውቃት አሜሪካዊቷ አቀንቃኝ ሪሀና፣ ለደህንነት በአመት ከ500,000 ዶላር በላይ ታወጣለች።
                      1. ቢዮንሴ
                      2.  
  • አሜሪካዊቷ ዘፋኝ፣ የዘፈን ደራሲ እንዲሁም ተዋናይት ቢዮንሴ፣ በአመት ከ2 – 4 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ታደርጋለች። እነዚህን እንደ ምሳሌ አነሳን እንጂ ለደህንነት ጥበቃ ሲባል ከግለሰብ እስከ የሀገር መንግስታት ጠንካራ ወጪ ይደረጋል። ለጦር መሳሪያዎች የሚወጣውን ወጪ ስንመለከት ፦
                1. F-35 Lightning II

  • ይህን የጦር መሳሪያ አጠናቆ ለማስረከብ ከ15 አመት በላይ የፈጀ ሲሆን፣ ዋጋው 5 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ይሆናል።
        1. Arleigh Burke DDG 51 Destroyer
        2.  

ይህ የጦር መርከብ በመጠኑ አነስ ያለ ሲሆን፣ በፍጥነት ትላልቅ መርከቦች የደህንነት ስጋት ሲኖርባቸው ደርሶ ጥበቃ የሚያረግ መርከብ ነው። ዋጋውም 843 ቢሊዮን ዶላር መሆኑ ተገልጿል።

          1. Virginia Class Submarine
  •  ይህ የባህር ወፍ-ክፍል ሰርጓጅ መርከብ 7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሚገመት ሲሆን በኑክሌር የተጎላበተ ሲሆን ባህርን ከስጋት ለመጠበቅ የተዘጋጀና የሚሳኤል ውንጨፋዎችን ጭምር ይከላከላል።

ምንጭ “moneyic.com

እስካሁን ባየናቸው ጥቂት ምሳሌዎች ብቻ ተመርኩዘን፣ ደህንነትን ማረጋገጥ ምን ያህል ምርጫ ውስጥ የማይገባ ጥያቄ መሆኑን መረዳት እንችላለን። ወደዋናው የጽሁፉ ሀሳብ ስንገባ፣ የሰው ልጅ ይሄን ያህል ራሱን ከጠላት ለመከላከል ወጪ ካወጣ፣ ራሱን ከራሱ ለመጠበቅ ምን ያህል ኢንቨስት አድርጎ ይሆን? ራሳችን የራሳችን ዋነኛ ጠላት ከመሆናችን ባለፈ፣ ከጠላቶቻችን የምንፈራውን ግድያ ሳይቀር የሰው ልጅ ራሱ ላይ እስከመፈጸም ይደርሳል። ገንዘብን ወጪ አድርገን መግዛት የምንችለው የደህንነት መሳሪያዎች ላይ ስንረባረብ፣ አትችዪም/ልም ፣ በቂ አይደለሽም/ህም ፣ ችሎታው የለሽም/ህም፣ እኔ እንድቀየር አሁን ያለው ወቅታዊ ሁኔታ መስተካከል አለበት እና የመሳሰሉትን እያልን ወደኋላ የሚያስቀረን ብሎም በራሳችን ወህኒ ውስጥ እድሜ ልክ ፍርደኛ የሚያረገን ከዛም ከባሰ ተስፋ አስቆርጦ ለዚ አለም ብቁ እንዳልሆንን አሳምኖ ራሳችንን የሚያስጠፋን በትሪሊዮን ዶላሮች ሊከላከሉት የማይችሉት ዋናው የሰው ልጅ ጠላት የሰው ልጅ ራሱ ነው። ታዲያ የራሳችን ጠላት የሆነው እኛን እንዴት ከራሳችን ማዳን እንችላለን በሚለው ርዕስ ላይ የጻፉት Leon F. Seltzer Ph.D. ካስቀመጡት ነጥቦች ውስጥ 5 ዋነኛ ሀሳቦች መርጬ ለማስፈር ሞክሪያለሁ።

            1. ራስን ከመተቸት ልማድዎ ይራቁ!

ምን ያህል ጊዜ እራስዎን ቁጭ አርገው ይገመግማሉ? በስህተቶችዎ እና ጉድለቶችዎ ላይ ያተኩራሉ፣ ወይም እንደማይሳካልዎ በመፍራት ከፈተናዎች ወደ ኋላ ይመለሳሉ? “Self-criticism” ሰዎች በልምምድ ከሚያገኙት የተሻለ ብቃት ይልቅ፣ ነገሮችን ያለምንም እንከን ለመስራት በሚፈጥሩት ውጥረት፣ አልችልም የሚል መንፈስን ከማላበስ በተጨማሪ ሙሉ ለሙሉ ስራ እስካለመስራት ይወስዳል። በተቻለን አቅም ለሰዎች ደግ መሆን አንዱ የህይወት መርህ እንደመሆኑ፣ ለራሳችንም ደግ መሆን መረሳት የሌለበት ጉዳይ ነው።

  1. አለም እንዴት እንደሚሰራ እና በዚህም እንዴት መስራት እንዳለቦት ያለዎትን ግምቶች እንደገና ይገምግሙ። አሁን ባለንበት ወቅታዊ ሁኔታ፣ አንዳንድ ጊዜ ወደ ተስፋ መቁረጥ እንድናመራ የሚያስገድዱ ኩነቶች ስንመለከት፣ አብዛኛው ማህበረሰብ ሰላማዊ ጊዜ እስኪመጣ በሩን ዘግቶ የሚጠባበቅ እንደሆነ ግልጽ ነው። ጥቂት ብልህ ሰዎች ግን የወቅታዊውን ችግር እንደ ልዪ አጋጣሚ በመመልከት፣ የሌሎቹንም ራስን ከጨዋታው ማግለል በመጠቀምም ጭምር በሚገርም ፍጥነት ወደ ትልቅ ደረጃ በመድረስ ላይ ያሉ እንዳሉ ያስተዋልነው ነው። ስለዚህም ጊዜው እስኪረጋጋ በማለት ራሳችንን የሚጎትተን ራሳችን ነንና ቢታሰብበት መልካም ነው።
  2. ላለፉት ጥፋቶች እራስዎን ይቅር ይበሉ።

ራስን ይቅር ማለት የምርጫ ጉዳይ ነው። ባለፉት ስህተቶቻችን እስረኛ ሆነን መኖር፣ ወይም ደግሞ ካለፉት ስህተቶቻችን ተምረን ነገ ላለመድገም መሞከር። “ዋናው ችግር ስለራስዎ ያለውን አመለካከት ማሸነፍ ነው። ያ ከሌለን በጭራሽ አናድግም። ራሱን ይቅር ያላለ ሰው ደግሞ መቼም ሌሎችን ማስተማር አይችልም!” -ማያ አንጅሎ

  1. የረዥም ጊዜ ቁጣን እና ንዴትን ያስወግዱ።

በሰዎች ዘንድ ተንቀናል፣ ተገለናል፣ ጉዳት ደርሶብናል፣ የምንወዳቸው ሰዎች አስቀይመውናል፣ ያመንኩት ክዶኛል፣ በተቸገርኩበት ሰአት አልደረሱልኝም፣ ወ.ዘ.ተ… እያልን ለረጅም ጊዜ በውስጣችን የያዝናቸው ቂም

እና ንዴት የሚፈጥሩት ውስጣዊ ቁጣ፣ ራሳችን እስካላጠፋነው ድረስ የሆነ ጊዜ ላይ ነበልባል የሚፈጥር የተዳፈነ እሳት ነው። ይህ ነበልባል ግን ለሌላ ጥቅም ከዋለ ብዙ ለውጦችን መፍጠር የሚችል ሀይል ነው። ስለዚህ ከዚ በኋላ እንደዚ አይነት ሁኔታዎችን እንደ ነዳጅ ሙሌት መመልከት አይከፋም።

  1. ነገሮችን በግል መውሰድ ያቁሙ (ወይም አስገቡት፣ ግን አትውሰዱት”)!

የአብዛኛው ማህበረሰብ ትችት የሚጀምረው ከራስ ከመነጨ ጉለት ነው። ቀድሞ በመተቸት ውስጥ ራስን መከለል የተለመደ ተግባር ነው። ስለዚህም ነው ነገሮችን በግል አለመውሰድ ራስን ከብዙ አላስፈላጊ ሀሳቦች ነፃ

ማውጣት ነው የሚባለው። የሰዎች ያልተገባ አስተያየት ያለኛ ምላሽ አቅም አልባ መሆናቸውን መገንዘብ ያስፈልጋል።

ግልጽ ነው! እነዚህ ነገሮች ለአፍ ቀላል ግን ለመተግበር አዳጋች ናቸው። አንድ ሀጥያቷን ልትናዘዝ የሀይማኖት አባት ጋር የሄድች እንስት ሀጥያቷን ለመናገር መፍራቷን ሲመለከቱ እንዲ አሏት ይባላል፣ “ሀጥያት እንዳለብሽ አምነሽ እኔ ጋር የመጣሽ ሰአት ነው ሀጥያትሽን ያሸነፍሽው!”። እናም ራሳችንን እንዳሰርንና የራሳችን ዋነኛ ጠላት መሆናችንን ያመንን ጊዜ ዋናውን ስራ ጨርሰናልና ቀጣዩን በሂደት ለማስተካከል መሞከር ተገቢ ነው።