Fitsum Atnafework K/Mariam

የዘራነውን ስንዘረዝር!

አንድ ቀን እለት አንድ ሆስፒታል ውስጥ ቁጭ ብዬ ተራ እየጠበቅሁ ሳለሁ ዘለግ ያለች ሴት የተጫማችውን ነጠላ ጫማ በድካም ስሜት እየጎተተች መጥታ ፊት ለፊቴ ተቀመጠች፡፡ ፊቷ አዲስ አልሆነብኝም፤ ግን ደግሞ እሷ ፊት ላይ ምንም “የት ነው የማውቃት?” መደናገር ስላላየሁባት የመልክ መመሳሰል አድርጌ ወስጄው በዝምታ እያለሁ ለየት ያለው ስሟ ከነአባቷ ሲጠራ ግምቴ ልክ እንደነበረ አመንኩ፡፡

የዘራነውን ስንዘረዝር! Read More »

ማህበራዊ ኃላፊነት እና የእራስ ኃላፊነት

ምን ሆነ መሰላችሁ! ሰሞኑን አንድ የቤተሰብ የምሳ ግብዛ ላይ አንድ ወጣት በትህትና ሲያስተናግድ ቆይቶ ለመሄድ ሊሰናበት ሲል ግብዣውን ያዘጋጁት ታላቅ ሰው ልጁን ለታዳሚዎች ማስተዋወቅ ፈለጉ፡፡ በጣም ጥሩ ልብ ያለው ልጅ መሆኑን፣ የዩኒቨርስቲ ምሩቅ መሆኑን እና ድግሱንም በደንብ ያገዘ መሆኑን አስተዋወቁና እስቲ እራስህን አስተዋውቃቸው በማለት እድሉን ሰጡት፡፡

ማህበራዊ ኃላፊነት እና የእራስ ኃላፊነት Read More »

ተጋልጠናል!

ማህበራዊ ሚዲያ (social media) ተጠቃሚ ከሚባሉ ሰዎች አንዷ ነኝ፡፡ በተለይ ፌስቡክ በጣም ጊዜ ካጣሁ እንኳን በቀን አንዴ ገብቼ ትንሽ መልእክት እጽፋለሁ፤ የሌሎችን ጽሑፎች አነባሁ፤ ሀሳብ እሰጣለሁ፣ እቀበላለሁም፡፡ ብዙ ሰዎች ፌስቡክን የስራ-ፈት ሚዲያ አድርገው ስለሚቆጥሩት እንደተዉት ሲናገሩ እሰማለሁ፡፡ እኔ ደግሞ በተቃራኒው ምንያህል እየተጠቀምኩበት እንደሆነ ቤቴ ይቁጠረው፡፡

ተጋልጠናል! Read More »

የእድገታችን ምስጢር?

እድገታችን የሚለው ቃል ሁላችንንም በሀሳብ በየአቅጣጫው እንደወሰደን አልጠራጠርም፡፡ የቱን እድገት ይሆን ደግሞ ዛሬ የምታወራልን፤ የሀገራችንን? የልጅነታችንን? የድርጅታችንን? እድገት በየፈርጁ በአእምሯን ውስጥ ተመላለሰ አይደል! እኔ ግን ማውራት የፈለግኩት የስራ ቦታ እድገት (promotion) ነው፡፡

የእድገታችን ምስጢር? Read More »

አግብታለች?

ስኬታማ ሴቶች የሆኑትን የሆኑት ብዙ ወድቀውና ተነስተው ነው! ለነገሩ ሴቶች ብቻ ሳይሆኑ ወንዶችም ጭምር፡፡ የእኔ ነገር በቀላሉ ሰዎች ብዬ እኮ ማጠቃለል እችል ነበር አይደል! ግን ማውራት የፈለግኩት ስለስኬታማ ሴቶች ገመና ነውና ነው፡፡ ወንዶች ስኬታማ ሲሆኑ ጎበዝ ነው፣ ባለሀብት ነው፣ ታድሎ፣ ከምን ተነስቶ ይሆን እዚህ የደረሰው፣ ወዘተ የመሳሰሉት እሱና እሱ ላይ ያተኮሩ አስተያየቶች እና አድናቆቶች ሲሰጡ ከመስማት ያለፈ ብዙም ስለ እሱ (ስለስኬታማው ሰውዬ) ግላዊ ማንነት ገፋ ተደርጎ ሲጠየቅ ወይንም ሲወራ አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ ቢጠየቅም ለአመል እንጂ ያንን ያህል እርቀት አይኬድም፡፡

አግብታለች? Read More »

conference

ትልቁ ኮንፈረንስ!

በሕይወቴ ብዙ የመጀመርያ እና አስደናቂ የሚባሉ ገጠመኞች ሞልተውኛል፤ በአብዛኛው ድንቅ የሚባሉ ሲሆኑ በተቃራኒውም ድንቅ ያልሆኑ ገጠመኞች አሉኝ፡፡ መጀመርያ ድንቅ ያልሆነውን አንዱን ልተርክላችሁ፡፡ ለረዥም ዓመታት የሰራሁበት እና በተለይ በወጣትነቴ ብዙ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ በማገልገል የምታወቅበት መሥሪያ ቤት በወቅቱ መሀከለኛው የአመራር ደረጃ ላይ ለነበርነው ኃላፊዎች በአውሮፓ ሀገራት የልምድ መጋራት እና የአጭር ስልጠና እድል ይሰጥ ነበር፡፡

ትልቁ ኮንፈረንስ! Read More »

እንደ ሁኔታው!

እንደ ሁኔታው! በአንድ ወቅት እሰራበት የነበረ አንድ ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት የመዋቅር ለውጦችን አደረገ እና ለረዥም ዓመታት ያገለገሉትን ሰራተኞች የአገልግሎት ዘመን ያላማከለ ስለነበር እጅግ አስቆጣቸው፡፡ በወቅቱ የነበረው የድርጅቱ ዋና

እንደ ሁኔታው! Read More »

እርቅ ከእራስ!

መቼስ እኛ ሰዎች ስንባል አንዱ መተዳደርያ ደንባችን በትንሹም በትልቁም ብስጭትጭት ማለት፣ መነጫነጭ፣ ማማረር የመሳሰሉት ጥቃቅን እና አነስተኛ ባህርያት ናቸው፡፡ እርግጥ ነው ስሜትን መግለጽ ሰውኛ ነው፡፡ ግን ደግሞ የእኛ ልምምድ ትንሽ በዘት ይላል፡፡

እርቅ ከእራስ! Read More »

ለውጥማ ያስፈራል!

የዛሬ ጽሑፌ መነሻ ሰሞኑን ከድሮ መ/ቤት ባልደረባዬ የተደወለልኝ ስልክ ነው፡፡ ይህቺ የሥራ ባልደረባዬ ደውላ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ በተለያየ ሚዲያ እያየችኝ እንደሆነ እና እድገቴ እንደሚያስገርማት በመግለጽ አድናቆቷን ካርከፈከፈችልኝ በኋላ ጨዋታውን አደራነው፡፡ አመስግኛት ሳበቃ ስለቤተሰብ፣ ስለ ሥራ ወዘተ ተጠያየቅን፤ ወግ ነውና፡፡ ይህች የቀድሞ የሥራ ባልደረባዬ ስትደውልልኝ ተጠንቅቄ ነው የማናግራት፤ ከቀድሞ ባህርይዋ በመነሳት፡፡ የፈለገውን ዓመት ፈጅቶ ባገኛት ምንም የተሻሻለ የባህርይ ለውጥ የማይታባት ናት፡፡ አሁንም እዚያው ከእኔ በፊት ተቀጥራ የምትሰራበት መ/ቤት እየሠራች መቆየቷ ነው መሰለኝ የተግባቦት ስልቷ አልተለወጠም፡፡ የዚያ መ/ቤቱ ብቻ ሳይሆን የባህርይዋም ታማኝ እና ቅን አገልጋይ እንበላት ይሆን!? በደወለችባቸው ወይም ባገኘኋት አጋጣሚዎች ሁሉ ታጉረመርማለች፡፡

ለውጥማ ያስፈራል! Read More »

Scroll to Top