3 6 9

Manifestation(መገለጥ) ምንድነው? ይሰራል ወይ? ከ 3፣6፣9 በስተጀርባ ያለው ሚስጥር ምን ይሆን?
እንደዚህ ሳይራቀቅና ብዙ ጥናቶች ሳይደረጉበት በፊት የሀገሬ ሰው የአፍህን ፍሬ ትበላለህ ሲል ብዙ ሰምተናል። በክርስትናም እምነት አንኳኩ ይከፈትላችኋል እንደሚል ቃሉ፣ manifestation አዲስ ግኝት ያልሆነና ያለም የነበረም ሚስጥር ነው። እዚህ ምድር ላይ በሰው እጅ የተፈጠሩ ነገሮች ሁሉ በመጀመሪያ በሰው አይምሮ ውስጥ የተፈጠሩ ነገሮች ናቸው። አንድ ሰው ቤት ወይም መኪና መግዛት ፈልጎ ግን ያ ሰው ያለው ገንዘብ አንዱንም ምኞቱን ሊያሳካለት ካልቻለ፣ እንዲ ማረግ ፈልግ ነበር ግን አቅሙ ስለሌለኝ ሊሳካልኝ አይችልም ብሎ ያመነ ሰአት ያንን ምኞቱን እንዳልፈለገው ተደርጎ ይቆጠራል። Law of attraction ወይም የስበት ህግ እንዲሁም Manifestation ወይም መገለጥ የሚሰሩት በማመን ወይም ባለማመን ውስጥ ነው። Manifestation ለመጠቀም ብዙ ስልቶች ያሉ ሲሆን ከነዛም ውስጥ የ Nikolas Tesla የ 3፣6፣9 ሚስጥርን በመጠቀም manifest ማረግ ይቻላል። ከዚም ተያይዞ የ Abraham Hicks “The 17sec rule of law of attraction” በመመልከት ምን ያህል የManifestation ሃይል መጨመር እንደምንችል እንመለከታለን።

Nikola Tesla ማነው?
Nikola Tesla ታዋቂ የሰርቢያን አሜሪካዊ ዜግነት ያለው ሲሆን የኤሌክትሪካል እና ሜካኒካል መሀንዲስ፣ በስራውም ከ300 በላይ የፈጠራ ስራዎች የፈጠራ ባለቤትነት በስሙ ያለ ሊቅ ነበር። Nikola Tesla በዋናነት የ AC motor ግኝት ባለቤትና AC generation and transmission technology development እውቀት ባለቤት ነው። 80% የሰው ልጅ ያገኛቸው ግኝቶች በሱ ግኝቶች ላይ የተመረኮዙ እንደሆኑ ይነገራል። ታዲያ ይህን ሰውና Manifestation ምን አገናኛቸው? Nikola Tesla ስለ 3፣6፣9 ሚስጥር ሲያብራራ እንዲ ብሎ ይጀምራል፣ “የ 3፣6፣9 ቁጥርን ሚስጥር ብታቁ የዚ አለም ቁልፍ ታገኙት ነበር።”። ስለነዚ ቁጥሮች የሂሳብ ህግ ለማስረዳት ረዘም ያለ ጊዜና ጥናት ስለሚፈልግ እንዴት ይህንን ሚስጥር ለManifestation መጠቀም እንደምንችል እንመለከታለን።

Abraham Hicks እና 17 ሰከንድ?

ይህ ህግ እንደሚያሳየው አንድን ምኞት ወደኛ ለመሳብ የሚያስፈልገን ትኩረት ወይም ተመስጦ 17 ሰከንድ እንደሆነ ነው። ይህ 17 ሰከንድ የዛን ሀሳብ vibration(ንዝረት) ያስጀምረዋል። እያንዳንዱ እዚ አለም ላይ ያለ ነገር ከ frequency እና vibration ጋር ግንኙነት እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ። የዛ vibration(ንዝረት) መጀመር ደግሞ ለስበት ሀይልን እንዲጀምር በር እንደመክፈት ነው። በAbrham Hicks ህግ አንድን ህልምና ምኞት ወደ እውነታ ለመቀየር 68 ሰከንድ ያለምንም ሀሳብ መበታተን ያንን ነገር መመኘት በቂ እንደሆነ ሲያስረዳ፣ ሆኖም ግን ያለምንም የሀሳብ መበታተን አንድን ነገር በተመስጦ ለማሰብ ለሰው ልጅ እጅጉን ከባድ ነው። ሆኖም ለሰው ልጅ አመቺ እንዲሆን ተደርጎ በ4 ጊዜ ድግግሞሽ ተግባር ላይ እንዲውል የተደረገ ሚስጥር ነው።

እንዴት ይህንን የ17 ሰከንድ Manifestation ቴክኒክ ስራ ላይ እናውለው?

⦁ ማግኘት የሚፈልጉትን መምረጥ
⦁ እንዲኖሮት የሚፈልጉትን ስሜት የሚያመጣልዎትን አዎንታዊ ሀሳብ ይምረጡ
⦁ ለ 17 ሰከንድ በሃሳብዎ ላይ ያተኩሩ
⦁ ይህንን የ17 ሰከንድ ትኩረት ለ3 ጊዜ ይደጋግሙት
⦁ ሀሳቡን በመልቀቅ ወደ ቀን ተቀን ስራ መመለስ

በመቀጠልም የ3፣6፣9 ሚስጥር እንመልከት
አንድን ክብ አምጥተን ምንም ያህል ጊዜ ብንከፋፍለው 3፣6፣9 ውጪ አይሆንም

 

ቁጥር 3
⦁ እራስን ማሳካት፣ ፈጠራ፣ ራስን መግለጽ እና ወደ ሙሉ ክብ የሚመጡ ነገሮች ያመለክታል።
⦁ ራዕይን የማቅረብ ሃላፊነት ያለው የእውቀት ሶስት ማዕዘን

ቁጥር 6
⦁ ሚዛን
ቁጥር 9
⦁ resolution(መፍትሄ)
በአጭሩ መግለጽ እንደተሞከረው የነዚ ቁጥሮች ሚስጥር ወደ manifestation ስናመጣዎ
⦁ ያንን manifestation ጠዋት ሶስት ጊዜ መጻፍ
⦁ ከሰአት 6 ጊዜ መጻፍ
⦁ ማታ 9 ጊዜ መጻፍ

በተጨማሪም ከላይ እንደተጻፈው የምንጽፋቸውን አረፍተ ነገሮች 17ሰከንድ በሚፈጅ ጊዜ መባል እንዲችሉ በማረግ የበለጠ እንዲሳኩ ማገዝ የሚቻል ይሆናል። እነዚ የmanifestation አረፍተ ነገሮች
⦁ አሁን ላይ እንደሆኑልን አርገን መጻፍ ይኖርብናል (ይህ ነገር ስለተደረገልኝ ደስተኛ ነኝ፣ ዛሬ ይህን ህልሜን አሳካሁ)
⦁ በወረቀትና በስኪብርቶ መጠቀም ይመከራል በዲጂታል መጻፊያዎች ከመጠቀም
⦁ ሁሌም አመስጋኝ መሆንን አለመርሳት

ይህ ጽሁፍ ለጥናቶች መንገድን እንደሚከፍት አምናለሁ። አመሰግናለሁ።