የእማማ በርሜል

“እድሜያችን አጥሮ ሳይሆን አብዛኛውን ጊዜያችንን እናጠፋለን። የፈለግንበት ቦታ እንድንደርስ በቂ እድሜ ተሰቶን ነበር በአግባቡ ብንጠቀምበት።”Seneca። ጊዜን በአግባቡ መጠቀም ስንል ምን ማለታችን ነው? የወርቅን ዋጋ ስናውቀው ከሁሉም ጌጦች ለይተን እንደምንጠብቀው ሁሉ፣ የጊዜን ዋጋ ማወቅ ስንችል ነው እንዴት በአግባቡ እንጠቀመው ሚለው ሀሳብ የሚመጣልን። የጊዜ አጠቃቀም ላይ ጉልበትን ማፍሰስ እውቀትን፣ ገንዘብን፣ ጤናን፣ ግንኙነትን እንዲሁም የውስጥን ሰላም ለማገኘት ዋነኛው ቁልፍ ነገር ነው።
ትልቁ ጊዜያችንን በአግባቡ እንዳንጠቀም የሚያግደን ነገር ቢኖር “ምን መስራት ይሆን ያለብኝ፣ አሁን ከምሰራው ስራ ቀጥሎ ምን ልስራ?” የሚለው ጥያቄ ነው። አንድን ስራ በጥሞና እየሰራን ከማሳካት ይልቅ ገና መስራት ስላለብን ስራ በማሰብ የአይምሮአችንን አቅም እናወርዳለን። ይህንንም ለምስቀረት ሁሌ ለምናረገው ነገር routine ሊኖረን ይገባል።
1. የጠዋት ሩቲን
1.1. ጽሞና(Silence)
1.2. ስለተደረገልን ነገር ማመስገን (Affirmation)
1.3. ምናብ(Visualization)
1.3.1. እንዴት ቀናችንን ማሳለፍ እንዳለብን ማሰብ
1.3.2. ምን ማሳካት እንዳለብን ማወቅ
1.4. የሰውነት እንቅስቃሴ(Exercise)
1.5. ንባብ(Reading)
1.5.1. ህልማችንን እና ማረግ ምንፈልገውን ጮክ ብሎ ማንበብ
1.6. መጻፍ (Scribing)

2. ለተገደበ ሰአት ያለምንም መረበሽ ስራን መስራት
2.1. ትኩረት
2.2. በየመሀሉ ለራስ እረፍት መስጠት
2.2.1. እረፍቶቻችን ትኩረት ሚያሳጡ መሆን የለባቸውም። ለምሳሌ ማህበራዊ ድህረገጾችን መጠቀም።

3. ትኩረት አርገን ምን ላይ መስራት እንዳለብን ማወቅ
3.1. ይህ ሁኔታ ቀላል ቢመስልም ሆኖም ግን ብዙሀን ሰዎች ሚሰሩትን ባለማወቃቸው ጊዜአቸውም ልክ ሳይሆን ልክ መስሎ በሚታያቸው ነገር ላይ ያጠፋሉ።
4. ሁል ጊዜ “To do List” ከመጻፍ ይልቅ ለአንድ ቀን ማሳካት ያለብን አንድ ትልቅ አላማ ይኑረን
4.1. ጠቃሚ ያልሆኑ ግን ሁሌም ስራ በዝቶብኛል የምንላቸውን እንዳስወግድ
5. 80/20 ህግ መከተል
5.1. 80% የሚሆነውን ጊዜያችሁን ራሳችሁ ላይ አጥፉ
5.2. የተቀረውን 20% ሌሎች ሰዎች ሂወት ላይ በምታስፈልጉበት ሰአት ላይ አጥፉ ለምሳሌ ኢሜል መመለስ
5.2.1. ኢሜል መመለስ ትልቅ ስራ እየሰራን ያለን ቢያስመስለንም ያ ግን ሀሰት ነው።

\"\"

\"\"

ከላይ የምታዩትን ሰንጠረዥ በመጠቀም ከላይ ለመግለጽ የተሞከሩትን ነጥቦች ላይ መስራት እንችላለን።

አንድ ማልረሳውን ታሪክ ላጫውታችሁ። አንድ ጎረቤቴ የሆኑ እናት ነበሩ። እኚህም እናት በደና ጊዜ መሬት ይያዙ እንጂ ከቅንጥብጣቢ የጡረታ ደመወዝ ውጪ ምንም ገቢ ያልነበራቸው ነበሩ። ታዲያም እኚህ እናት ቤት ሁሌ ጠብ ጠብ የሚል ቧንቧ እና ትልቅ በርሜል ነበራቸው። እሳቸው ቤት በሄድኩ ቁጥር ሁሌም እሱን ቧንቧ ሳየው ተበላሽቶ ማሰራት ስላቃታቸው እንደሚንጠባጠብ አስብ ነበር። አንድ ቀን ግን እንዲህ አልኳቸው፣ “እማማ፣ ይሄን ቧንቧ እኔ ላሰራልዎት ነገ ቤት ይዋሉ ቧንቧ ሰሪውን ይዤ እንድመጣ።”። እሳቸውም አይ አንቺ ሞኝ በሚል አይነት ፈገግ ብለው አዩኝ። “ምነው እማማ፣ ምን አጠፋሁ?” ነበር ጥያቄዬ የሳቸውን ምንም መልስ ሳልሰማ። እማማ እንዲ ብለው ቀጠሉ፣ “አይ ልጄ፣ እኔኮ አውቄ ነው ሀይል ሳይኖረው ጠብ ጠብ እንዲል ብቻ የማደርገው።”። “እንዴ ለምን?”፣ መልሱን የማወቅ ጉጉቴ ጨምሯል። “የውሀ የምከፍለው ገንዘብ እንዳይኖር ነዋ! ጠብ ጠብ ሲል የውሀ ቆጣሪው ዉሀ እንደተከፈተ አያውቅም። ስለዚህ የሄው ቧንቧውም እድሜ ልኩን ይንጠባጠባል፣ እኔም ከስር ከስሩ እየቀዳሁ እጠቀማለሁ።”። የእኚህን እናት ብልህነት ያየ የሂወት ትርጉምን ማየት ይችላል። ከላይ በነጥቦች ልንዘረዝረው የሞከርነው የጊዜ አጠቃቀም በአንድ ቀን ሂወታችንን ሊቀይር አይችልም። ልክ እንደ እማማ በርሜል ቀስ እያለ ይሞላል እንጂ።