ያለመሞከር ልምድ ነው?
በዘመኑ አጠራር አንድ ባለሀብት ዘመድ አለችኝ፡፡ ባለሀብት ድሮ ድሮ ዲታ፣ ሞጃ፣ ሀብታም ይባል እንደነበረው፡፡ እና ይቺ ዘመዴ አንዱ የሀብቷ መጠን መለክያ በጣም አዲስ የሆነ ቴክኖሎጂ ውጤት ተጠቃሚ በመሆኗ ነው፤ በተለይ […]
በዘመኑ አጠራር አንድ ባለሀብት ዘመድ አለችኝ፡፡ ባለሀብት ድሮ ድሮ ዲታ፣ ሞጃ፣ ሀብታም ይባል እንደነበረው፡፡ እና ይቺ ዘመዴ አንዱ የሀብቷ መጠን መለክያ በጣም አዲስ የሆነ ቴክኖሎጂ ውጤት ተጠቃሚ በመሆኗ ነው፤ በተለይ […]
እንዲያው አጋነንሽ አትበሉኝ እና (ከፈለጋችሁም በሉኝ) አንዲት ሴት እና አንድ ወንድ ተመሳሳይ ገድል ቢሠሩ ቀድሞ የሚወደሰው ወንዱ ነው፡፡ ቀድሞ መወደስ ብቻ አይደለም ገዝፎ የሚወደሰውም እሱ ነው፡፡ ይሄንን ያልኩት በተለያዩ አጋጣሚዎች ስላስተዋልኩ ነው፡፡
ባለፈው ቅዳሜ ፌብሩዋሪ 18 ቀን 2023 (እ.አ.አ.) ኤውብ “ጓደኝነትን ማክበር” በሚል ርእስ የእኔ እና የጓደኛዬን የነባት አባስን በኤውብ ቆይታችን ያካበትነውን የአሥር ዓመታት ጓደኝነት በማክበር እኛም ይህንኑ ምስጢር ለሌሎች እንድናጋራ እድል ተሰጥቶን ነበር፡፡ በቅድምያ መልካም ግንኙትን የምታበረታታው ብቻ ሳይሆን የምታከብረውን ማህበራችንን፣ በዋናነት ደግሞ ይህንን ሀሳብ ያፈለቀችውን የማህበራችን መሥራች ናሁን እኔና ጓደኛዬ እጅግ አናመሰግናታለን፡፡ ኤውብ እንደ ሙያ ማህበር ሙያተኛ ሴቶችን ለማስተሳሰር እያደረገች ያለችው ጥረት ተሳክቶላታል፡፡ ብዙዎች ጓደኛ ሆነዋል፣ ከዚያም ባለፈ የሥራ አጋር ሆነዋል፡፡ እስቲ ስለ እኔና ስለ ጓደኛዬ ነባት የኤውብ ጓደኝነት እና ምስጢራችን ቅዳሜ እለት ላልተገኛችሁትም ሆነ ኤውብን የበለጠ ለማወቅ ለምትሹ ላውጋችሁ፡፡
የአሥር ዓመታት የጓደኝነት ምስጢር Read More »
የዋኋ የሥራ ባልደረባዬ¡ አንዲት የቀድሞ የሥራ ባልደረባዬ ከረምረም ብላ ከቆየች በኋላ ስልክ ትደውልና ሞቅ ደመቅ ያለ ሰላምታ ትሰጠኛለች፣ ቤተሰቤን በሥማቸው እያስታወሰች ደህንነታቸውን ትጠይቀኛለች፣ ታደንቀኛለች፣ ታሞጋግሰኛለች፤ ከዚያ በደንብ ካሟሟቀችኝ በኋላ “እኔ
የዛሬ ጽሑፌን መነሻ ሀሳብ የወለደልኝ አብረን ሰርተን ለዓመታት ሳላገኛት ኖረን በቅርብ ቀን ያገኘኋት የሥራ ባልደረባዬ ናት፡፡ ይህቺ ሴት አብረን ስንሠራ በጣም አስገራሚ ባህርይ ነበራት፡፡ በተለይ አለቃ/ኃላፊ ለፀብ ከፈለጋችሁ የመረጃው ምንጭ እሷ እንደምትሆን ከጀርባዋ ይወራ ነበር እና ከሠራተኞች በቡና ወይንም በማንኛውም ሁኔታ ልትቀላቀል ስትመጣ “ጨዋታ ቀይሩ!?” ይባል እንደነበር አልረሳውም፡
እንኳንም አገባሁ! ፍፁም አጥናፈወርቅ ኪ/ማርያም መቼስ የእኛ ማህበረሰብ አዛኝ ነው፤ ማለቴ ያው ሴት ልጅ ስትዳር ማየት ያስደስተዋል፡፡ ከተዳረች በኋላ ደግሞ ስትወልድ፤ ከዚያም ጾታ እያሰባጠረች ደጋግማ ስትወልድ፡፡ እናም ለአቅመ ትዳር ደርሳለች