Fitsum Atnafework K/Mariam

እየሞከርኩ ነው!

ሰሞኑን በጣም በብዙዎች የታየ፣ የተወደደ እና መነጋገርያ የሆነ ቪዲዮ ለዛሬ ጽሑፌ ከነርእሱ መነሻ ሆኖኛል፡፡ ላላያችሁት ግን ትንሽ ስለቪዲዮው ልንገራችሁ፡፡ አንድ አከራይ ተከራዩን መንገዱ ላይ ጠብቆ የቤት ኪራይ ሳይከፍል በመዘግየቱ እንዲከፍል ሲያስታውሰው ግራ የተጋባው ተከራይ ምርር ብሎ ሳይከፍል የዘገየበትን የተደራረበ ችግር የሚናገርበት አባባል ነው፤ “እየሞከርኩ ነው!” ማለቱ፡፡ ሁላችንም ችግሮቻችንን ለማሸነፍ እየሞከርን ነው፡፡ ግን ደግሞ ችግርን የሚቀርፍ ወይንም ፈቀቅ አድርጎ እና እፎይታ የሚያስገኝ ሙከራም እያደረግን ለመሆኑ ብዙዎቻችን እርግጠኞች አይደለንም፡፡ ታድያ “ሙከራችን ምን አይነት ቢሆን ነው?”

እየሞከርኩ ነው! Read More »

በጋመ ምጣድ ለመጋገር ወረፋ አንያዝ!

አቤት የድሮ ጉርብትና እኮ ብዙ ደሳስ የሚሉ ትውፊቶች ነበሩት። ማህበራዊ ኑሮው በተለይ ዳግም ላይመለስ የጠፋ እንደ ትርክት ለልጆቻችን የምናወራው ለእኛ ብቻ ትዝታው የሚያስደስተን:፡ ለምሳሌ እንዲህ እንደአሁኑ በከተማችን ብዙ የኤሌክትሪክ ምጣደች በየቤቱ ባልነበሩበት ዘመን የጋራ የሆኑ የጭስ ኩሽናዎች ነበሩ፡፡

በጋመ ምጣድ ለመጋገር ወረፋ አንያዝ! Read More »

ወንዶች እና ቀለበት

በስራዬም በትምህርት ቤቶቼም ያፈራኋቸው ድንቅ ድንቅ የሁኑ የወንድ ጓደኞች አሉኝ፡፡ ወንዶች ለጓደኝነት በጣም ይመቻሉ፡፡ ጓደኝነት ስል ግልጽ ለማድረግ ጾታዊ ንክኪ የሌለበት ጓደኝነት ወይንም በተለምዶ ወንድም ጓደኛ ማለት ነው፡፡ በተለይ በአንድ ርእሰ ጉዳይ ላይ ለመወያየት ያወቁትን እና የገባቸውን በግልብ ያለማለባበስ ለማስረዳት ምንም ወደኋላ አይሉም፡፡ እንደዚያ ማለቴ ደግሞ ሴት ጓደኞች አይመቹም እያልኩ እንዳልሆነ ያሉኝ የሴት ጓደኞች ብዛት ምስክር ነው፡፡ አሁን ለማውራት የፈለግኩት ስለግልጽ ውይይት ነው፡፡ በተለይ እኛ ሴቶች ብዙ ነገር እንደ ነውር (taboo) እየተቆጠረብን ሀሳባችን ተቆነጣጥሮ የሚቀርብበት ይበዛል መሰለኝ፤ ማለቴ መሰለኝ ስል ያው ጥርጣሬ ነው፡፡ እና ግልጽ ውይይት የምንፈራው ወደንና ፈቅደን ሳይሆን ማህበረሰቡ የሰራን በሽፍንፍን እንድንወያይ ነው ለማለት ነው፡፡

ወንዶች እና ቀለበት Read More »

እያለን የለንም!

እያለን የሌለው ምን ይሆን ብላችሁ ከጠየቃችሁኝ ካለን ነገር ብጀምር በጣም ብዙ ነገር አለን፡፡ ብዙዎቻችን በተወሰነ መልኩ ትምህርት ቤት የሄድን፣ በተለያዩ ስራዎች እና ንግድ ላይ የተሰማራን፣ ከሰዎች ጋር የምንኖር እና የምንሰራ፣ ከሰዎች ልምድም እውቀትም የምንጋራ የምንማማር ሰዎች ነን፡፡ ብዙዎቻችን አእምሮ አለን፤ የምናስብበት፣ የምንተሳሰብበት፣ የምናሰላበት፣ የምንሰላበት፡፡ ከአእምሮ በተጨማሪ የስሜት ሕዋሳቶች አሉን፤ አካባቢያችንን የምናይበት፣ የምናዳምጥበት (ካዳመጥን…በኋላ እመለስበታለሁ)፣ ሚዛን የምንጠብቅበት፣ የምንዳስስበት፣ የምንንቀሳቀስበት፣ የምንቀምስበት እና የምንለይበት፡፡ እነዚህ የግል ንብረቶቻችን ሲሆኑ እንደማህበረሰብ ደግሞ ባህል፣ ኃይማኖት፣ ማህበራዊ ኑሮ፣ ሀገር፣ መንደር፣ ወዘተ አሉን፡፡ አንድ ሰው በዚህ ሁሉ መኖር ውስጥ ታድያ እንዴት ነው አቅም እና አቋም እንደሌለው ሆኖ የሚገኘው!?

እያለን የለንም! Read More »

የአበባየሽ ወይ ገራሚ እይታ!

መስከረም አንድ ቀን የሚከበረው የኢትዮጵያ አዲስ አመት የአንድነት አውድአመት ነው፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘር እና ኃይማኖት ሳይለይ የሚያከብረው እና በደስታ የሚቀበለው፡፡ ሁላችንም ልጅ አዋቂው እንኳን ለ2018ዓ.ም. በሰላም ደረሰኝ የምንባባልበት ትልቅ ቀን ነው (በዚሁ እንኳን አደረሰን ብያለሁ!)፡፡ እለቱም እንቁጣጣሽ ተብሎ በተለይ ታዳጊ ሴቶች ልጆች “አበባ አየሽ ወይ!” ብለው እየዞሩ ይጨፍራሉ፤ ሳይርቁ በጎረቤቶች እና በሚያውቋቸው ሰዎች ቤቶች፡፡ ታድያ ዛሬ በዚህ ጉዳይ የሚያስወራኝ ገጠመኝ ስለኖረኝ እንጂ አዲስ አመትማ ሁላችንም የምናውቀው እና የምናከብረው ነውና እያስተዋወቅኳችሁ እንዳልሆነ ይሰመርበት፡፡

የአበባየሽ ወይ ገራሚ እይታ! Read More »

እናጣራ!

የመጪውን የኢትዮጵያ 2018 ዓ.ም. በትዳር ለመጀመር የአቀዱ ተጣናጆች ሰሞኑን ሽምግልና እየላኩ ነው፡፡ ትዳር ደግሞ ታቅዶ ሲጀመር ፍጻሜው ያማረ ይሆናል አይባልም ለካ፤ ምክንያቱም ትዳር የ80 ዓመት ውል ስለሆነ ቀድመን የምንፈጸመው እኛ ስለሆንን (መሰለኝ)! ዋናው ቁምነገር የታቀደ ነገር ካልታቀደ እና ከግብታዊ ውሳኔ በብዘ እጥፍ ይሻላል፡፡ ታድያ ስናቅድ በጀት ነክ ነገሮችን እንደ ሰርግ፣ የቤት ኪራይ፣ የልጆች ብዛት፣ የቤት ቁሳቁስ ወዘተ ብቻ አይደለም ማቀድ ያለብን፤ ብዙ ከእቅድ ጋር ተጓዳኝ ይሁኑ አይሁኑ ባይታወቅም ብቻ መጠናት ወይንም መጤን ያለባቸው ጉዳዮች አሉ፡፡

እናጣራ! Read More »

ድምጽ አልባው ጦርነት

ይሄ ማህበራዊ ሚዲያ በጣም ብዙ ጥቅም ያለውን ያህል ጎጂነቱም ቀላል እንዳይመስላችሁ፡፡ እኔ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ እንደመሆኔ መጠን አንዳንዴ የፈለግኩትን ብቻ እያጣራሁ እና እያጠለልኩ ሳይሆን ከነድፍድፉ የምጋፈጥበት ሁኔታ አሌ አይባልም፤ ምክንያቱም አልጎሪዝሙ ክሊክ አድርጌ የምመርጠውን ብቻ ሳይሆን ያልመረጥኩትን ጭምር ስለሚያቀርብልኝ ነው፡፡ ደግሞ ሰዎች አይደለን እንጓጓለን፤ “ካመጣው ለምን አላይ አልሰማ!?” ብለን፡፡

ድምጽ አልባው ጦርነት Read More »

ሙስና ወይንስ ጉቦ!?

የስራ ዘመኔን ወደኋላ ሄጄ ሳስታውስ በጣም የሚናፍቁኝ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ከሰው ጋር አብሮ እንደመስራት ድንቅ ትምህርት ቤት አለ ይሆን!? እኔ በጭራሽ የለም ነው የምለው፡፡ ለምን መሰላችሁ ትምህርት ቤት (ኮሌጅ እና ዩኒቨርስቲን ጨምሮ) የምንማረው በተግባር የሚወርደው ተቀጥረን ስንሰራ ወይንም የራሳችን ድርጅት ኖሮን ቀጥረን ስናሰራ ነው፡፡ እዚህ ውስጥ ደግሞ እንደ ቀስተደመና ቀለም የተዥጎረጎርን ሰዎች አለን፤ የድርጅቱን አላማ ለማሳለጥ (በአዲሱ አባባል) የምንጣመር፡፡

ሙስና ወይንስ ጉቦ!? Read More »

ዶሮ ፊት ፈንግል ካልተወራ ልጆች ፊትስ?!

መቼስ አባቶቻችን ተረት ሲያውቁ እኮ! ቆይ ግን ይቅርታ አባቶቻችን ብቻ ነበሩ እንዴ የሚተርቱት? ጀመረኝ ደግሞ ዋና ሀሳቤን ገና ሳልዳስስ የተረት እና ምሳሌ ታሪካዊ አመጣጥ የአባቶች ወይንስ የእናቶች ወደሚለው ዥው ብዬ ገባሁ፡፡ ብቻ የድሮ ተረቶች አስተማሪዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ በርእሱ ያነሳሁት “ዶሮ ፊት ፈንግል አይወራም” የሚለው መቼስ ዶሮዎች ጆሮ ስላላቸው አይደለም፤ ሰውኛ አባባል ሆኖ እንጂ እኛን ለማስተማር፡፡ የዚህ አባባል አንዱ ግጣሙ ልጅ ፊት የማይወሩ ነገሮችን እንዳናወራ የሚያስታውስ ይመስለኛል፡፡ እርግጥ ነው ታማሚ ፊትም ስለሞት አይወራም፡፡

ዶሮ ፊት ፈንግል ካልተወራ ልጆች ፊትስ?! Read More »

የ 15 ዓመት ባለልደቷ ጉብል ገራችኝ!

በሕይወታችን ውስጥ አቅጣጫ በማስያዝ፣ በመምከር፣ በመዝከር፣ በመደገፍ፣ እንዲሁም በመገሰጽ ትልቅ ድርሻ ያላቸው ሰዎች በአብዛኛዎቹ ታላላቆቻችን ናቸው፡፡ ምክንያቱም ከተኖረ ሕይወታቸው ቆርሰው ስለሚሰንቁልን፡፡ አንዳንዶች አሉ ወጣቶች ሆነው ታናናሾች ሆነው የታላላቆችን ሚና የሚጫወቱ፤ ሕይወት መቀየር ብቻ አይደለም የመኖርን ትርጉም ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ፡፡

የ 15 ዓመት ባለልደቷ ጉብል ገራችኝ! Read More »

Scroll to Top