Fitsum Atnafework K/Mariam

እኩልነት ለምኔ!

የማርች ወር መቼስ ሴቶች በአንድ ጣራ ስር በብዛት የምንታደምበት ወር ነው፡፡ ደስ ያሰኛል! ቢያንስ በአመት እንዲህ አምሮብን፣ ተሳክቶልን፤ በጀት ተበጅቶልን (ውሳኔ ሰጪው በአብዛኛው ያኛው ጾታ ነው ብዬ ነው) የልብ የልባችንን ማውራት ቀላል ነገር እንዳይመስላችሁ፡፡ በዚህ አጋጣሚ አቅልላችሁ ለተመለከታችሁት ወንድሞች እና እህቶች ይቅር በሉኝና ተሳስታችኋል የምል ነኝ (ስለይቅርታችሁ አመሰግናለሁ!)፡፡ አንዳንዶችማ “በየአመቱ ተመሳሳይ ነገር ለማውራት ቢሰበሰቡት ምን ዋጋ አለው፣ ከስብሰባ ያለፈ ተግባር አናይም፣ ለይስሙላ ነው፣ ወዘተ” በሚል መንፈስ ድከም ብሏቸው ሌላውንም ሰው ያዳክማሉ፡፡

እኩልነት ለምኔ! Read More »

አትሞገሽ ያላት ፍጡር!

ሰው የሚለው ስያሜ ውስጥ ሁለታችንም አለን፤ ሴቶችም ወንዶችም፡፡ ነገር ግን ለአገላለጽ ስንጠቀመው ሰው የሚለውን ስያሜ በወንድ እንጠቀልለውና ሴቶችን እንዘላቸዋለን፤ ማለቴ እኛ ሴቶች እንዋጣለን፡፡ ለምሳሌ “ሰው መጣ” ስንል የመጣችው/የመጣው ሴት ወይንም ወንድ ሊሆን ይችላል፡፡ ያኔ ነበር ከመነሻው “ለምን?” ብለን መጠየቅ የነበረብን፡፡ ምክንያት ካላችሁኝ ኋላ ላይ ልመለስበት፤ አይሻልም? ወይንም ሳልመለስም ቢሆን ሀሳቤ ይገልፀው ይሆናል፡፡ ከዚያ በፊት ግን እንኳን ለአድዋ የድል መታሰብያ እና ለማርች የሴቶች ወር አደረሰን! ወቅቱ የአድዋ ድል የሚዘከርበት እና ተከትሎም የማርች ወር የሴቶች እኩልነት ይረጋገጥ በሚል ብዙ መድረኮች የሚዘጋጁበት እና እኛም የምንሳተፍበትም አይደል፤ እኮ!

አትሞገሽ ያላት ፍጡር! Read More »

አማጭ-አዋጭì

ትዳር ከሚመሰረትበት መንገድ አንዱ በአማጭ በኩል የሚደረግ መጣመድ (matchmaking)  ነው። “እከሌና እከሊት ቢጋቡ ጥሩ ይጣነዳሉ” ብሎ/ላ በጥሩ መንፈስ የተነሳሳ ሰው ለሁለቱ ተጣናጆች እንዲተያዩ፣ እንዲተዋወቁ ሁኔታውን ሲያመቻቹላቸው ማለት ነው። በቅን ልቦና ተነሳስተው እራሳቸውን የአማጭ መንበር ላይ ያስቀመጡ ሰዎችን የማደንቅ ነኝ፤ እኔ በግሌ፡፡

አማጭ-አዋጭì Read More »

አልሞተችም!

በዚህች ምድር ላይ ስንኖር መቼስ ይሆናል ካልነው ይልቅ አይሆንም ያልነው እየሆነ ማየትን ተለማምደነዋል፡፡ ይሄ ግጥምጥሞሽ ሲደጋገም ነው ከእኛ በላይ ሌላ ትልቅ አዛዥ ናዛዥ፣ ተቆጣጣሪ እና ወሳኝ ኃይል እንዳለ የማንጠራጠረው(የማልጠራጠረው በሚለው ይታረምልኝ)፡፡ ለነገሩ እኮ ሕይወትም የሚያጓጓው የገመትነው ሳይሆን ቀርቶ በድንገቴ (surprise) በመታጀቡ ነው፡፡ ታድያ ክፉውን ድንገቴ ያርቅልን!

አልሞተችም! Read More »

አትተኙ!

እስቲ ስንቶቻችሁ ናችሁ “የሕይወቴ ቅኝት” የሚለውን መጽሐፍ ያነበባችሁ? ያላነበባችሁ እንግዲህ ተዋውሳችሁ አንብቡ ምክንያቱም ሁለተኛ እትም ለማሳተም “እቁብ ግቡልኝ?” ብዬ ጓደኞቼን በዚህ ዘመን አላስቸግርም፡፡ ድሮ የእኛ ዘመን፣ የእነሱ ዘመን ስንል አስር ወይንም ሃያ ዓመት ልዩነት እየፈለግን ነበር፤ ምክንያቱም ለውጦች አዝጋሚ (evolutional change) ናቸዋ፡፡ አሁን እኮ ዘመን ወደ ሳምንት ተቀይሯል መሰለኝ ባለፈው ሳምንት የነበረ ዛሬ ተለውጦ ታገኙታላችሁ፡፡ ነገር ሁሉ እንደቤት አስቤዛ ተለዋዋጭ ሆኗል፡፡ የዛሬ ሦስት ዓመት በኤውብ እቁብተኞቼ ድጋፍ አሳትሚያለሁ፡፡ እና ኑሮ ቀልብ ባሳጣበት እና አንባቢ በጠፋበት በዚህ ዘመን ወደ ማተምያ ቤት አልሄድም ለማለት ነው፡፡ ለማንኛውም መጽሐፌን ያነሳሁላችሁ ከዚያ ውስጥ አንዱን ሰበዝ መዝዤ ላወራላችሁ ፈልጌ ነው፡፡

አትተኙ! Read More »

ትዳራችን ኮሽታ የለውምì

ድሮ ወደ ኮሌጅ ልገባ ስል ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወደ ኮሌጅ ለመሄድ የሚያዘጋጅ መጽሐፍ ነው ተብሎ የታመነበትን የሲሳይ ንጉሱ ድርሰት የሆነውን “ሰመመን” አንብቤ እንድዘጋጅ ያደረጉትን የጓደኛዬ የገነት ወንድሞች በሕይወቴ ክብር መዝገብ ላይ ጽፌአቸዋለሁ፡፡ አስባችሁታል ገና ዩኒቨርስቲውን ዋና በር ስትረግጡ በስህተትም ተብላችሁ የማታውቁትን “እንዳንቺ አይነት ቆንጆ ሴት በዚህ ምድር አይቼ አላውቅም!” የሚሏችሁ ሲኒየር ተማሪዎች ሙድ እየያዙባችሁ እንደሆነ አይገባችሁም ነበር እኮ፡፡

ትዳራችን ኮሽታ የለውምì Read More »

እርጉዟን ማን ይቅጠራት!?

እርጉዟን ማን ይቅጠራት!? Image source: https://www.pngegg.com/en/png-besfc/download አንዳንድ የጦፉ ክርክሮች በአንድ ወገን አሸናፊነት ወይም አሳማኝነት ሳይቋጩ ሲቀሩ እንዴት ያንገበግበኛል መሰላችሁ፡፡ በጓደኛሞች ወይም በቤተሰብ መሀከል የሚደረግ ክርክር ወይም ቃሉን የተሻለ ለማድረግ ጭውውት

እርጉዟን ማን ይቅጠራት!? Read More »

ጆሮም እንደ ዓይን መዝጊያ ቢኖረው?!

የሰውነት አካላችን በቅንጅት የሚሰራው ስራ እኛን እኛ ያደርገዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለነገሮች ተጋላጭ የሚያደርገን ፈልገን ሳይሆን ሳንፈልግ ወይንም ከአቅም በላይ በሆነ ክስተት ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ቦታ ሄደን ለተከሰተው ክስተት እግራችን ፈቅዶ ባይሄድ ላናይ ላንሰማ እንችል ነበር፡፡ በሄድንበት ቦታ ዓይናችን “ይሄን ማየት አልፈልግም” ብሎ ከጨፈነ ያንን ክስተት ባለማየት እንተርፋለን ማለት ነው፡፡ እጃችንም ከመንካት ከታቀበ ታቀበ ነው፡፡ ብቻ በአብዛኛው የሰውነታችን ክፍል እምቢ የማለት መብት እስኪኖረው ድረስ ነው የተሰደረው፡፡ አፍንጫ እንኳን እድሜ ለኮቪድ አይባልም እንጂ ልብስ ተሰፍቶለታል፡፡

ጆሮም እንደ ዓይን መዝጊያ ቢኖረው?! Read More »

ትዳር ለእሷ እና ለእሱ

ሕይወትን በሁለት ትላልቅ ምእራፎች ከፍለን እንድናወጋ ፈለግሁ እና ይህንን ጽሑፍ ጫር ጫር አደረግሁ፤ የሚመለከተንም የማይመለከተንም ካነበብን በኋላ የእኛ ሕይወት የቱ ጋር እንደሆነ ቆም ብለን እንድናይ ያመላክተናል ብዬ አምናለሁ፡፡

ትዳር ለእሷ እና ለእሱ Read More »

ሽፍንፍን!

እንደ ሀገር ብዙ ጥሩ ጥሩ የሆኑ ባህሎች እና ትውፊቶች ያሉን ዜጎች ነን፡፡ እንደ ሰው የምንረዳዳባቸው የምንደጋገፍባቸው አበረታች የሆኑ እሴቶቻችን የትዬለሌ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን ኑሮ ቢከፋ (ቢወደድብን)  “ከእኔ ችግር የእነሱ ይብሳል” ብሎ የተቸገሩትን የሚዳብሱ እና የሚያጎርሱ ዜጎች ያለባት ሀገር ናት፣ ኢትዮጵያ፡፡

ሽፍንፍን! Read More »

Scroll to Top