መረጃ
በአገር አቀፍ የሴቶች የኢኮኖሚክ ኢምፓወርመንት ፎረም ላይ ምርታቸውን በኤግዚቢሽን ላይ የሚያቀርቡ ነጋዴ ሴቶች ስም ዝርዝር እንዲላክልን ስለመጠየቅ

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሴቶችና የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ፤ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፤ በኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት የሴቶች ክፍል አስተባባሪነት እ.ኤ.አ 29 ኤፕሪል 2ዐ22 የሴቶች የኢኮኖሚክ ኢምፖወርመንት ፎረም ተቋቁሞል፡፡ የፎረሙ ዓላማ የሴቶች ኤኮኖሚክ ኢምፖወርመንት በተመለከተ የሚያጋጥሙ ችግሮች ላይ በመወያየት የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው፡፡ ምሥረታው የተከናወነው በአዳማ ከተማ ሲሆን በከተማው የሚገኙ ነጋዴ ሴቶች ምርታቸውን በኤግዚቢሽኑ ላይ በማቅረብ እና በመሸጥ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ሁለተኛው የፎረሙ ጉባዔ የሚካሄደው በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን በዚህ ጉባዔ በአዲስአበባ የሚገኙ ነጋዴ ሴቶች ምርታቸውን ኤግዚቢሽኑ ላይ በማቅረብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የእስትሪንግ እና የቴክኒካል ኮሚቴው ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡
በመሆኑም መረጃውን ለነጋዴ ሴቶች እንድታደርሱልን የተለመደ ትብብራችሁን እየጠየቅን ፍላጐት ያላቸው ከዚህ በታች በተገለፀው ሠንጠረዥ ሞልተው እስከ ሚያዝያ 19 ቀን 2ዐ15 ድረስ በኢሜይል titiliyew@yahoo.com እና በስልክ ቁጥር 0911234984 እንዲያሳውቁን እንዲደረግ እንጠይቃለን፡፡
ተ.ቁ | የድርጅት ስም | የተሳታፊ ስም | የምርት ዓይነት | ስልክ ቁጥር | ኢሜይል |
ከሰላምታ ጋር
የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት